ለፓኪስታን የመጀመሪያውን ወርቅ ያስገኘው አትሌት የጀግና አቀባበል ተደረገለት
ፕሬዝደንት አሲፍ አሊ ዛርዳሪ ናዲም ላስመዘገበው ስኬት የፓኪስታን ሁለተኛው ከፍተኛ የሲቪሊያን ሽልማት ይበርከትለታል ብለዋል
የ27ቱ ናዲም በፓሪስ በተካሄደው የጦር ውርወራ ውድድር 92.97 ሜትር በመወርወር ከዚህ በፊት አሸናፊ የነበረውን ህንዳዊውን ኒራጅ ቾፕራን አሸንፏል
ለፓኪስታን የመጀመሪያ ወርቅ ያስገኘው አትሌት የጀግና አቀባበል ተደረገለት።
በፓሪስ እየተካሄደ ባለው ኦሎምፒክ በጦር ውርወራ ለፓኪስታን የመጀመሪያውን የወርቅ ያስገኘው ፓኪስታናዊ አትሌት አርሻድ ናዲም ሀገሩ ሲገባ በሺዎች የሚቅጠሩ ሰዎች የጀግና አቀባቀል አድርገውለቻል።
አትሌቱ በምስራቃዊቷ ከተማ ላሆር ሲደርስ" ረጅም እድሜ ለአርሻድ ናዲም፣ ፓኪስታን ለዘላለም ትኑር" የሚል የአበባ ጉንጉን ያጠለቁለትን አባቱን ጨምሮ ከቤተሰቦቹ ጋር ተገናኝቷል።
የ27ቱ የሁለት ልጅ አባት የሆነው ናዲም በፓሪስ በተካሄደው የጦር ውርወራ ውድድር 92.97 ሜትር በመወርወር ከዚህ በፊት አሸናፊ የነበረውን ህንዳዊውን ኒራጅ ቾፕራን አሸንፏል።
በፑንጃብ ግዛት በጭቃ ቤት የወለደው የናዲም ማሸነፍ በኢኮኖሚያዊ ቀውስ እና እየጨመረ ባለው የታጣቂዎች ጥቃት ምክያት ችግር ውስጥ ለምትገኘው ሀገር አስገራሚ ሆኗል።
ፕሬዝደንት አሲፍ አሊ ዛርዳሪ ናዲም ላስመዘገበው ስኬት የፓኪስታን ሁለተኛው ከፍተኛ የሲቪሊያን ሽልማት ሂላል-አይ-ኢምታይዝ ይበርከትለታል ብለዋል።
"ፈጣሪን አመሰግነዋለሁ። ቤተሰቦቼን እና የፓኪስታን ህዝብን አመሰግናለሁ" ሲል ናዲም ለተሰበሰበው ህዝብ ተናግሯል።
"ከውጤቱ ጀርባ በእኔ እና በአሰልጣኜ ሳልማን ቡት ጠንካራ ስራ ነበር" ብሏል ናዲም።