የፓኪስታን ፍርድ ቤት በዋትስአፕ ላይ መልእክት ባጋራ ተማሪ ላይ የሞት ቅጣት አስተላለፈ
ስም ማጥፋት በፓኪስታን ሞት የሚያስቀጣ ወንጀል ነው
በሀገሪቱ ፑንጃብ ግዛት የሚገኘው ፍርድ ቤት ተማሪው እስልምና እምነት ተከታዮችን ለማስቆጣት በማሰብ ፎቶዎችን እና ቪዲዮዎችን አጋርቷል ብሏል
የፓኪስታን ፍርድ ቤት በዋትስአፕ ላይ መልእክት ባጋራ ተማሪ ላይ የሞት ቅጣት አስተላለፈ።
የፓኪስታን ፍርድ ቤት በዋትስአፕ መተግበሪያ ላይ "ስምአጥፊ" መልእክት አጋርቷል ባለው አንድ ተማሪ ላይ የሞት ቅጣት ማስተላለፉን ቢቢሲ ዘግቧል።
በሀገሪቱ ፑንጃብ ግዛት የሚገኘው ፍርድ ቤት ተማሪው የእስልምና እምነት ተከታዮችን ለማስቆጣት በማሰብ ፎቶዎችን እና ቪዲዮዎችን አጋርቷል ብሏል።
ከዚህ በፊት የ17 አመት ልጅም በተመሳሳይ ጥፋት የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት ነበር። ነገርግን ሁለቱም ፍርደኞች ድርጊቱን አልፈጸምንም ሲሉ አስተባብዋል።
ስም ማጥፋት በፓኪስታን ሞት የሚያስቀጣ ወንጀል ነው። አንዳንድ ሰዎች ከመከሰሳቸው በፊት ከፍተኛ ድብደባም ይደርስባቸዋል።
ተማሪው የሞት ቅጣት እንዲጣልበት ምክንያት የሆነውን ቅሬታ የቀረበው በላሆር በሚገኘው የፓኪስታን ፌደራል ኢንቨስቲጌሽን ኤጀንሲ ስር ያለው የሳይበር ክራይም ዩኒት ነው።ጉዳዩም ወደ ፍርድ ቤት እንዲተላለፍ ተደረገ።
ፍርድ ቤቱ ያሳለፈው ውሳኔ እንደሚለው የ22 አመቱ ተማሪ የነብዩ መሀመድን እና ሚስቶቻቸውን የሚያንቋሽሹ ፎቶዎችን እና ቪዲዮዎችን በማዘጋጀቱ የሞት ቅጣት ተፈርዶበታል።
በእድሜ ትንሹ ተከሳች ደግሞ የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበታል።
ተከሳሹ ግን ከተለያዩ ቁጥሮች እነዚህን ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች መቀበሉን ተናግሯል። ኤጀንሲውም የተከሳሹን ስልክ መመርመሩን እና እነዚህ ነውር የሆኑ መልእክቶች እንደተላኩለት አረጋግጧል።
የተከሳሾቹ ጠበቃ ግን ሁለቱ ተጠርጣሪዎች "በሀሰት ክስ ወጥመድ ውስጥ ገብተዋል" የሚል መከራከሪያ አቅርቧል።
የሞት ቅጣት የተላለፈበት ልጅ አባት ለላሆር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማለታቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
ሁለተኛው ተከሳሽ ግን በእድሜ ትንሽ በመሆኑ ምክንያት የእድሜ ልክ እስር እንደተፈረደበት ፍርድ ቤቱ ገልጿል።