የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢራን በብሪቲሽ-ኢራን ዜጋ ላይ የፈጸመችውን የሞት ቅጣት አወገዙ
የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢራን በብሪቲሽ-ኢራን ዜጋ ላይ የፈጸመችውን የሞት ቅጣት አወገዙ
ኢራን የቀድሞ የመከላከያ ሚንስትር የነበሩት አሊሬዛ አክባሪ ለብሪታንያ በመሰለል ወንጀል የሞት ፍርድ ከተፈረደባቸው ከቀናት በኋላ መገደላቸውን አስታውቃለች
ብሪታንያ የኢራንን የሞት ቅጣት ውሳኔ አወገዘች
የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ኢራን በብሪታኒያ-ኢራናዊ ዜጋ ላይ የፈጸመችውን የሞት ፍርድ “የፍርሀት ድርጊት” ሲሉ አውግዘዋል።
ጠቅላይ ሚንስትሩ የኢራንን መንግስት “በአረመኔ አገዛዙ ሰብዓዊ መብት እየገረሰሰ ነው” በማለት አውግዘዋል።
ኢራን የቀድሞ የመከላከያ ሚንስትር የነበሩት አሊሬዛ አክባሪ ለብሪታንያ በመሰለል ወንጀል የሞት ፍርድ ከተፈረደባቸው ከቀናት በኋላ መገደላቸውን አስታውቃለች።
ሱናክ በትዊተር ገጻቸው ላይ "በኢራን የብሪታኒያ-ኢራናዊ ዜግነት ያለው አሊሬዛ አክባሪ መገደል አስደንግጦኛል። ሀሳቤ ከአሊሬዛ ጓደኞች እና ቤተሰቦች ጋር ነው" ብለዋል።
የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጀምስ ክሌቨርሊ ግድያውን ተከትሎ መግለጫ ያወጡ ሲሆን፤ ድርጊቱ በዋዛ አይታለፍም ብለዋል።
"ይህ አረመኔያዊ ድርጊት በጠንካራ አነጋገር ውግዘት ይገባዋል። የኢራን አገዛዝ ለሰው ልጅ ህይወት ያለውን ግድየለሽነት በድጋሚ አሳይቷል" በማለት ወቅሰዋል።
"በኢራን ድርጊት መጸየፋችንን ግልጽ ለማድረግ የኢራኑን አምባሳደር እንጠራለን። ሀሳባችን ከአክባሪ ቤተሰብ ጋር ነው" ሲሉ አክለዋል።
ሚዛን የዜና አገልግሎትን ጠቅሶ አናዶሉ እንደዘገበው አክባሪ የተገደሉት በ"በሙስና" እና "በሀገሪቱ የውስጥ እና የውጭ ደህንነት ስጋት ላይ በመጣል" በሚል ወንጀል ነው ።