ተጎጂዎች `አረብ ኢምሬትስ አስፈላጊ በሆነ ሰዓት ሁሉ ከፍሊስጤማውያን ጎን ያለች ሀገር ነች` ብለዋል
በጋዛ የሚገኙ የተጎጂ ቤተሰቦች ለተደረገላቸው ድጋፍ አረብ ኢምሬትስን አመሰገኑ።
አል አይን ኒውስ በጋዛ ውስጥ በሚገኙ ሆስፒታሎች ተገኝቶ ተጎጂዎችን ያጋገረ ሲሆን፤ በዚሁ ጊዜም ፍሊስጤማውያኑ ለአረብ ኢምሬትስ ድጋፍ ምስጋናቸውን ገልጸዋል።
ፍሊስጤማውያኑ፤ `አረብ ኢምሬትስ አስፈላጊ በሆነ ሰዓት ሁሉ ከፍሊስጤማውያን ጎን ያለች ሀገር ነች፤ ስደተኞችን በመርዳት እና መሰረታዊ የሆነ ለውጥ እንዲመጣ ያላሰለሰ ጥረት ስታደረግ መቆየቷንም` ገልጸዋል።
በጋዛ አንደ አዲስ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎም አረብ ኢምሬትስ ሲቪሎች ህይወት እንዲጠበቅ ተኩስ አቁም እንዲደረግና የእርዳታ ዘመቻ መጀመሯንም ለአብነት ጠቅሰዋል።
የተባበሩት አረብ ኢምሬት የመንግስት ሆስፒታሎች አንድ ሺህ ፍልስጤማዊያን ህጻናት እና ቤተሰቦቻቸው እንዲስተናገዱባቸው ወስናለች።
ይህንን ተከትሎም በጋዛ የሚገኘው የአል አቅሳ ሰማእታት ሆስፒታል ቃል አቀባይ ካህሊል አል-ዳክራን ለአል ዐይን አንደተናገሩት፤ የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ለህጻት የጤና ድጋፍ ልታደርግ ላሳለፈችው ውሳኔ እና ለህዝባችን ለምታደርጋቸው ድጋፎች ልናመሰግናት እንወዳለን ብለዋል።
ቃል አቀባዩ አክለውም “ሁሉም የአረብ፣ እስላማዊ ሀገራት እና በዓለም ላይ ያሉ ሁሉም ነፃ ሀገራት የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችን ተግባር እንዲከተሉ እንጠይቃለን” ብለዋል።
በሆስፒታሉ ውስጥ ህጻን ልጇን በማሳከም ላይ የነበረች ሳብሪ የተባለች እናትም፤ አረብ ኢምሬትስ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከልጆቻችን እና ከህዝባችን ጎን በመሆን ላደረገችልን ድጋፍ አመሰግናለሁ ብላለች።
የተባበሩት አረብ ኢምሬት የመንግስት ሆስፒታሎች አንድ ሺህ ፍልስጤማዊያን ህጻናት እና ቤተሰቦቻቸው እንዲስተናገዱባቸው ወስናለች።
የአረብ ኢምሬት ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አልናህያን የመንግስት ሆስፒታሎች ፍልስጤማዊያን እንዲስተናገዱባቸው መወሰናቸውን የኢምሬት ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
የአረብ ኢምሬት ውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሼክ አብዱላህ ቢን ዛይድ አልናህያን ከዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ፕሬዝዳንት ሚርጃና ስፖሊያርች ጋር በስልክ ስለ ጋዛ ተጎጂዎች መወያየታቸው ተገልጿል።
ሀገሪቱ ፍልስጤማዊያን ህጻናት እና ቤተሰቦቻቸው በመንግስት ሆስፒታል የህክምና እና ሌሎች መሰረታዊ ድጋፎች ይደረግላቸዋልም ተብሏል።