አረብ ኢምሬትስ በጋዛ በሆስፒታል ላይ የደረሰውን ጥቃት አወገዘች
በሆስፒታሉ ላይ በደረሰው ጥቃት ከ500 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር ባለስልጣን ተናግረዋል
አረብ ኢምሬትስ በንጹሃን እና በሲቪል ተቋማት ላይ የሚደርሰው ጥቃት እንዲቆም በጥብቅ ጠይቃለች
አረብ ኢምሬትስ በጋዛ በአል አህሊ ባፕቲስት ሆስፒታል ላይ የደረሰውን ጥቃት አውግዛለች።
በሆስፒታሉ ላይ በደረሰው ጥቃት ከ500 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር ባለስልጣን ተናግረዋል።
የአረብ ኢምሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በጥቃቱ በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት ማዘኑን ገልጿል፤ በጥቃቱ ቤተሰባቸውን ላጡትም መጽናናትን ተመኝቷል።
ሚኒስቴሩ በንጹሃን እና በሲቪል ተቋማት ላይ የሚደርሰው ጥቃት እንዲቆም በጥብቅ ጠይቋል።
አረብ ኢምሬትስ ተጨማሪ የሰው ህይወት እንዳይጠፋ እና ግጭቱ ወደ ዌስት ባንክ እንዳይስፋፋ አለምአቀፍ ማህበረሰብ ተኩስ አቁም እንዲደረስ ጫና እንዲፈጥር ጥሪ አቅርባለች።
አረብ ኢምሬት ሀማስ በእስራኤል ላይ ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ባወጣችው መግለጫ ሁለቱም አካላት ግጭት እንዲያቆሙ መጠየቋ ይታወሳል።
ሀማስ በ50 አመታት ውስጥ ባደረሰባት ከባድ ጥቃት 1300 በላይ ዜጎቿን ያጣችው እስራኤል የእወሰደች ያለውን የአጸፋ ምላሽ አጠናክራ ቀጥላለች።
የአየር ድብደባ ስታደርግ የቆየችው አስራኤል በእግረኛ ጦር ጥቃት ለመፈጸም ጋዛን በመክበብ ዝግጅት በማድረግ ላይ ነች።
የሰሜን ጋዛ ነዋሪዎች የእስራኤልን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ ወደ ደቡብ አቅጣጫ ተሰድደዋል።