አረብ ኢምሬትስ 50 ሚሊዮን ድርሃም ዋጋ ያለው እርዳታ ለፍልስጤም እንዲሰጥ ወሰነች
ድጋፉ እንዲሰጥ የተወሰነው በመሃመድ ቢን ራሽድ አል መክቱም አለምአቀፍ ፋውንዴሽን ነው
የእራኤል እና ሀማስ ግጭት የሰብአዊ ቀውስ እንዲፈጠር አድርጓል
አረብ ኢምሬትስ 50 ሚሊዮን ድርሃም ዋጋ ያለው እርዳታ ለፍልስጤም ወገኖች እንዲሰጥ ወስናለች።
የእራኤል እና ሀማስ ግጭት የሰብአዊ ቀውስ እንዲፈጠር አድርጓል።
ድጋፉ እንዲሰጥ የተወሰነው በመሃመድ ቢን ራሽድ አል መክቱም አለምአቀፍ ፋውንዴሽን ነው።
የአረብ ኢምሬትስ ምክትል ፕሬዝደንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሁም የዱባይ ገዥ ቬህ መሃመድ ቢን ረሽድ አልመክቱም የ50 ሚሊዮን ድርሃም አስቸኳይ እርዳታ በሞሃመድ ቢን ረሽድ አልመክቱም አለምአቀፍ ኢኒሼቲብ አማካኝነት ለፍልስጤም እንዲሰጥ ውሳኔ አሳልፈዋል።
ድጋፉ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ላሉት ፍልስጤማውያን እንደሚሰጥ ተነግሯል።
አረብ ኢምሬትስ በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ያሉ ወገኖችን መርዳት አንዱ ፖሊሲዋ መሆኑን ገልጻለች።
ሀለቱም አካላት ግጭቱን እንዲያቆሙ ጥሪ ካቀረቡት ሀገራት ውስጥ አረብ ኢምሬትስ አንዷ ነች።
የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ የእስራኤልን ድንበር በመጣስ ከፍተኛ የተባለ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ በሁለቱም ወገን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል።
እስራኤል እየወሰደች ያለውን የአጸፋ ጥቃት አሁንም ቀጥላለች።
የሀማስ መቀመጫ የሆነችውን ጋዛን ከበባ ውስጥ በማስገባት ጥቃት እያደረሰች ነው፤ በሰሜን ጋዛ የሚኖሩ ሰዎችም በ24 ሰአታት ውስጥ ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች።
ተመድ ይህን የእስራኤል ውሳኔ ሰብአዊ ቀውስ ይፈጥራል ሲሉ ተቃውመዋል።