ፓንጎሊን የኮሮና ቫይረስ አስተላላፊ ሊሆን እንደሚችል ተመራማሪዎች ገለጹ
ፓንጎሊን የኮሮና ቫይረስ አስተላላፊ ሊሆን እንደሚችል ተመራማሪዎች ገለጹ
ገዳይ የሆነው ኮሮና ቫይረስ ከሌሊት ወፍ ወደ ሰው የተላለፈው በኤሲያ ውስጥ ለምግብነትና ለመድኃኒትነት በሚሸጠው ፓንጎሊን በሚባል አጥቢ እንሰሳ ሊሆን እንደሚችል ተመራማሪዎች መግለጻቸውን ስካይ ኒውስ ዘግቧል፡፡
ይህ ግኝት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ትልቅ ጥቅም እንዳለው ምርምሩን የሚመራው የደቡብ ቻይና ግብርና ዩኒቨርሲቲ በድረ-ገጹ አስታውቋል፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ እስከአሁን በኮሮና ቫይረስ 636 ሰዎች የሞቱ ሲሆን፣ 31000 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡
የአለም ጤና ድርጅት የጋውን፣ የጭምብል፣ የጓንና የሌሎች የመከላከያ መሳሪያዎች እጥረት እንደሚኖር አስጠቅቃቋል፡፡