መሳሪያው በአርካሪ አጥንቱ ላይ አጋጥሞት የነበረው ጉዳት እንዳይሰማው በማድረግ ቆሞ እንዲሄድ አስችሎታል
መንቀሳቀስ የማይችለው ስዊዘርላንዳዊ አእምሮ እና አከርካሪ አጥንትን በሚያገናኘው መሳሪያ በመታገዝ ቆሞ መሄድ ችሏል።
- የኤችአይቪ ቫይረስን ከሌሎች ጋር በጋራ ያገኙት ፈረንሳያዊ ሳይንቲስት አረፉ
- ለወንድ ልጅ መጸ’ነስ ምክንያት የሆነው የዋይ ክሮሞዞም በመጥፋት ላይ መሆኑን ሳይንቲስቶች ተናገሩ
ይህ ሰው መንቀሳቀስ ያቆም ከ12 አመታት በፊት ነበር።
መሳሪያው በአርካሪ አጥንቱ ላይ አጋጥሞት የነበረው ጉዳት እንዳይሰማው በማድረግ ቆሞ እንዲሄድ አስችሎታል።
ግሬት ጃን ኦስካም የተባለው ይህ ግለሰብ በፈረንጆቹ 2014 በቻይና በደረሰበት የሳይክል አደጋ አከርካሪው በመጎዳቱ እግሮቹ ሙሉ በሙሉ እና እጆቹ በከፊል መንቀሳቀስ አቁመው ነቀር።
ነገረግን ዛሬ ላይ በአእምርው እና በነርቮቹ መካከል በተገጠመው "ድጂታል ብሪጅ" አማካኝነት በመደገፊያ ምርኩዝ መንቀሳቀስ ችሏል።
ይህ መሳሪያ ኦስካም ለመሄድ ሲያስብ በእእምሮው ውስጥ ያሉት ኤሌክትሮዶች መልዕክቱን በአከርካሪው ላይ ወዳሉት ኤሌክችሮዶች መልዕክት ያስተላልፋሉ።
"አሁን ለምፈልገውን መስራት አችላለሁ፤ ለመራመድ ስሞክር መሳሪያው ይጀምራል።" ብሏል ኦስካም።
ከአምስት እስከ አሰር ደቂቃ ድረስ እግሬን መቆጣጠር እንደሚችል ኦስካም ተናግሯል።
ኦስካም መሳሪያው በህይወቱ ትልቅ ለውጥ እንዳመጣለት ይናገራል።
ኦስካም በፈረንጆቹ 2018 በቴክኖሎጂ በመታገዝ በኤሌክትሮኒክስ ግፊት የከርካሪ አጥንት ጉዳት ያለባቸው ሰዎች መንቀሳቀስ እንደሚችሉ የሚሳይ ጠንካራ የማስመሰል ስልጠና ወስዶ ነበር።
የኦስካም አከርካሪ በጭንቅላቱ ውስጥ ከተቀበረው እና የዲስክ ቅርጽ ካለው መሳሪያ ጋር በመቀናጀት እንቅስቃሴ መፍጠር መቻሉ ተመራማሪዎች ይገልጿሉ።