ፓሪስ ከ100 ዓመታት በኋላ በወንዞቿ ላይ ዋናን ፈቀደች
ፓሪስ ከ100 ዓመት በፊት በወንዞቿ ላይ ዋናን የከለከለችው በብክለት ምክንያት ነበር
የ2024 ኦሎምፒክ አዘጋጅ የሆነችው ፓሪስ የውሀ ዋናን በወንዞቿ ላይ መፍቀዷን የውድድሩ ማድመቂያ ይሆናል ተብሏል
የፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ ከ100 ዓመታት በኋላ በወንዞቿ ላይ ዋናን ፈቀደች።
የፈረንሳይ ዋና ከተማ የሆነችው ፓሪስ ከአንድ ክፍለ ዘመን በኋላ ዜጎቿ በወንዞቿ ላይ እንዲዋኙ ልትፈቅድ መሆኑን ገልጻለች።
ሴን የተሰኘው ወንዝ በፓሪስ ትልቁ ወንዝ ሲሆን ከዚህ በፊት የከተማዋ ነዋሪዎች የሚዋኙበት ታዋቂ ወንዝም ነበር።
ይሁንና ወንዙ ለዋና መፈቀዱ ብክለትን አስከትሏል፣ የከተማዋንም ውበት እየጎዳ ነው በሚል ፈረንጆቹ 2023 ላይ ክልከላ ተጥሎበት ቆይቷል።
ይሁንና የከተማዋ አስተዳድር 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዩሮ በጀት መድቦ ባካሄደው የማጣሪያ ፕሮጀት ወንዙ ከ100 ዓመት በኋላ ዳግም ለዋና ዝግጁ መደረጉን ሲኤንኤን ዘግቧል።
ከአንድ ዓመት በኋላ በሚካሄደው የፓሪስ ኦሎምፒክ የዋና ውድድሮች በዚሁ ወንዝ ላይ እንደሚካሄድም ተገልጿል።
ከውድድሩ በኋላም የወንዙ መዋኛ ስፍራዎች ለከተማዋ ነዋሪዎች እና ጎብኚዎች ክፍት እንደሚሆኑ የፓሪስ ከተማ ከንቲባ ተናግረዋል።
የመዋኛ ስፍራዎቹ ከፓሪስ ኦሎምፒክ በኋላ ለህዝብ ክፍት ይሆናሉ መባሉ ወደ ፓሪስ የሚያቀኑ ጎብኚዎችን ቁጥር እንደሚያሳድገው ተገልጿል።
ፓሪስ ወንዞቿን ከብክለት ለመከላከል የወሰደቻቸው እርምጃዎች ከወዲሁ ትኩረትን የሳበ ሲሆን በብክለት ምክንያት ከተሞቻቸው የተጎዱባቸው ሌሎች የአውሮፓ እና እስያ ከተሞች ልምድ የመውሰድ ፍላጎት እንዳደረባቸው በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።
ፓሪስ ከተማ በአውሮፓ ብዙ ጎብኚዎች ከሚያዘወትሯቸው ከተሞች መካከል ከቀዳሚዎቹ ተርታ ትሰለፋለች።