ወንዙ ንጹህ መሆኑን ለማሳየት የዋኘችው ከንቲባ
የፓሪስ ኦሎምፒክ አድማቂ ይሆናል የተባለው ወንዝ ዜጎች ንጹህ አይደለም እያሉ ይገኛሉ
የከተማዋ ከንቲባ የወንዙን ንጽህና ለማረጋገጥ ወደ ወንዙ ገብተው ዋኝተዋል
ወንዙ ንጹህ መሆኑን ለማሳየት የዋኘችው ከንቲባ
የፈረንሳይ ዋና ከተማ የሆነችው ፓሪስ ከአንድ ክፍለ ዘመን በኋላ ዜጎቿ በወንዞቿ ላይ እንዲዋኙ ልትፈቅድ መሆኑን ገልጻለች።
ሴን የተሰኘው ወንዝ በፓሪስ ትልቁ ወንዝ ሲሆን ከዚህ በፊት የከተማዋ ነዋሪዎች የሚዋኙበት ታዋቂ ወንዝም ነበር።
ይሁንና ወንዙ ለዋና መፈቀዱ ብክለትን አስከትሏል፣ የከተማዋንም ውበት እየጎዳ ነው በሚል ፈረንጆቹ 2023 ላይ ክልከላ ተጥሎበት ቆይቷል።
ይሁንና የከተማዋ አስተዳድር 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዩሮ በጀት መድቦ ባካሄደው የማጣሪያ ፕሮጀክት ወንዙ ከ100 ዓመት በኋላ ዳግም ለዋና ዝግጁ መደረጉን ሲኤንኤን ዘግቧል።
ፓሪስ ከ100 ዓመታት በኋላ በወንዞቿ ላይ ዋናን ፈቀደች
ይሁንና የፓሪስ ከተማ ነዋሪዎች ወንዙ ንጹህ አይደለም በሚል እንደማይዋኙ መናገራቸውን ተከትሎ የከተማዋ ከንቲባ አኒ ሂዳልጎ በዋና ልብስ በወንዙ ላይ ሲዋኙ ታይተዋል፡፡
እንዲሁም የፓሪስ ኦሎምፒክ ዝግጅት ሀላፊ ቶኒ ኢስታንጉትም ከንቲባዋን ተከትለው በወንዙ ላይ ሲዋኙ ታይተዋል፡፡
ተጠባቂው የፓሪስ ኦሎምፒክ ከአንድ ሳምንት በኋላ የሚጀመር ሲሆን ጎብኚዎች እና ተሳታፊዎች አስቀድመው ወደ ፈረንሳይ መጓዝ ጀምረዋል፡፡
ይሁንና ፈረንሳዊያን የሀገራቸውን መንግስት ለመቃወም በወንዙ ላይ እንደሚጸዳዱ እየዛቱ ሲሆን የሀገሪቱ የደህንነት ተቋማት ጥብቅ ጥበቃ ለማድረግ መሰማራታቸው ተገልጿል፡፡