“ስማችን ተነሳ የሚሉ አካላት ለምን ህዝብ በዚህ ደረጃ ፈረጀን የሚለውን ነገር ራሳቸውን መመርመር ያስፈልጋል”- ፈቃዱ ተሰማ
ምርጫ ቦርድ ወደፊት ሊፈጸሙ የሚችሉ ተመሳሳይ ድርጊቶችን በመከታተል እጩዎችን እስከመሰረዝ የሚደርስ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል ማሳሰቡ የሚታወስ ነው
የኦሮሚያ ብልጽግና ጽህፈት ቤትኃላፊው ከሰሞኑ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተካሄዱ ሰልፎችን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል
የኦሮሚያ ብልጽግና ከሰሞኑ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የተካሄዱትን የድጋፍ ሰልፎች በተመለከተ መግለጫ ሰጠ፡፡
መግለጫውን የሰጡት የፓርቲው ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማ ህዝቡ ለአመራሩ እና ለፓርቲው ላሳየው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡
ጽህፈት ቤት ኃላፊው ጽንፈኝነት ከየትም መጣ ከዬት ህዝብን የማይወክል መሆኑን በግልጽ ለማሳየት የተደረገ ሰልፍ ነው ያሉም ሲሆን የለውጡን ቀጣይነት እና አመራሩን ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየበት እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
ሰልፉ አብሮነቱን፣ አቃፊነቱን እና አንድነቱን ያሳየበት ነው ያሉም ሲሆን ህብረብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጵያን ለመገንባት ያለውን ፍላጎት ለማሳየት የተደረገ እንደሆነም በመግለጫው ጠቁመዋል፡፡
ህዝብ በራሱ ፍላጎት ለሰልፍ መውጣቱን የገለጹት አቶ ፍቃዱ ከ25 እስከ 30 ሚሊዬን የሚጠጋ ህዝብ ወጥቷል ብለዋል፡፡
በዚህ ደረጃ የወጣ ህዝብ በገባው ልክ ጉዳዮችን ሊያነሳ ይችላልም ነው ጽህፈት ቤት ሃላፊው ያሉት፡፡
ስማችን ተነሳ የሚሉ አካላት ለምን ህዝብ በዚህ ደረጃ ሊፈርጃቸው እንደቻለ በራሳቸው ሊመረምሩ ይገባልም ብለዋል፡፡
የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ቢያከብሩም እና ጉዳዩ በራሱ መድረክ የሚታይ ቢሆንም ሚዛናዊ መሆን አለበት የሚል የግል አቋም እንዳላቸው ተናግረዋል፡
የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) በሰልፎቹ ላይ ከተንጸባረቁት የፍረጃ እና የማውገዝ መልዕክቶች ጋር በተያያዘ ምርጫ ቦርድ እርምጃ እንዲወስድ በደብዳቤ መጠየቁ ይታወሳል፡፡