"ገነት አስገባችኋለሁ" በሚል ከአማኞች ገንዘብ የተቀበለው ናይጄሪያዊ ፓስተር ተከሰሰ
የናይጄሪያ ክርስቲያን ማህበር በበኩሉ የግለሰቡን ሀይማኖታዊ እውቅና አንስቷል
ፓስተር አዴ አብርሃም ከአማኞች 750 ዶላርን ይቀበል ነበር ተብሏል
"ገነት አስገባችኋለሁ" በሚል ከአማኞች ገንዘብ የተቀበለው ናይጄሪያዊ ፓስተር ተከሰሰ፡፡
በናይጄሪያ ኢቫንጀሊስት ቤተክርስቲያን የሀይማኖት ሰባኪ ወይም ፓስተር የሆነው አዴ አብርሃም አማኞችን በማታለል ወንጀል ተከሷል፡፡
የምዕራብ ናይጄሪያው ፓስተር የተከሰሰው አማኞችን መግቢያውን አውቃለሁና ወደ ገነት አስገባችኋለሁ በሚል ገንዘብ በመቀበሉን ተከትሎ ነው፡፡
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ፓስተር አዴ ለአገልግሎቱ እስከ 310 ሺህ የናይጄሪያ ኔይራ ወይም 750 ዶላር ከአንድ አማኝ ይቀበል ነበር፡፡
ይህን ማድረጋቸውን የሚሳይ ጥቆማ የደረሰው የሃገሪቱ ፖሊስ በፓስተሩ ላይ ምርመራውን መጀመሩ ተገልጿል፡፡
ወንዶችና ሴቶች የተለያየ ቋንቋ የሚናገሩባት የናይጄሪያዋ ‘ኡባንግ’ መንደር
የ19 የአሜሪካ እና የካናዳ ዩኒቨርሲቲዎችን የትምህርት ዕድል ያሸነፈችው ናይጄሪያዊት
ፖሊስ 750 ዶላር ለፓስተሩ ከከፈለ አንድ ግለሰብ የቀረበለትን አቤቱታ መነሻ በማድረግ ወደ ፓስተር አዴ ቤተክርስቲያን አምርቶ ቃል መቀበሉን ዘገባው አክሏል፡፡
ፓስተር አዴም ወደ ገነት የሚያስገባውን በር እንደሚያውቁ ለአማኞች መናገሩን አምኗል፡፡ ሆኖም ገንዘብ ተቀብሏል መባሉን አልተቀበለም፡፡
በዚህ ድርጊት ማዘኑን የገለጸው የናይጄሪያ ክርስቲያን ማህበር በበኩሉ ለፓስተሩ የሰጠውን ሀይማኖታዊ ማዕረግ ማንሳቱን ገልጿል፡፡
በናይጄሪያ ሀይማኖትን መሰረት ያደረጉ የተለያዩ የማታለያ ድርጊቶች በመታየት ላይ ሲሆኑ የሀገሪቱ ፖሊስም በአታላይ አገልጋዮች ላይ ምርመራ በማድረግ ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡