ልዩልዩ
ፕሬዚዳንት ካጋሜ የኮሮና ክትባት የወሰዱ የመጀመሪው የምስራቅ አፍሪካ መሪ ሆኑ
በሩዋንዳ እስካሁን ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች የኮቪድ 19 ክትባን ወስደዋል
ሩዋንዳ እስከ 2021 መጨረሻ 30 በመቶ ዜጎቿን ለመከተብ እቅድ ይዛለች
የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ እና ባለቤታቸው ቀዳማዊት እመቤት ጃኔት ክትባቱን ሲወስዱ የሚያሳይ ፎቶግራፍም በሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ይፋዊ ትዊተር ገጽ ላይ ተለቋል። ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ የኮሮና ክትባት የወሰዱ የመጀመሪያው የምስራቅ አፍሪካ መሪ ሆነዋል፡፡
እስካሁንም በሩዋንዳ ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች የኮቪድ 19 ክትባን መውሰዳቸውም በትዊተር ገጹ ላይ ተመላክቷል።
ሩዋንዳ 100 ሺህ ዶዝ ፋይዘር እና 240 ሺህ ዶዝ አስትራ ዜንካ ክትባቶችን የተረከበች ሲሆን፥ እስከ 2021 መጨረሻ 30 በመቶ እንዲሁም እስከ 2022 መጨረሻ ደግሞ 60 በመቶ ዜጎቿን ለመከተብ እቅድ ይዛለች።
በሩዋንዳ እስካሁን 200 ሺህ ዜጎቿ ላይ የኮሮናቫየረስ የተገኘ ሲሆን 271 ዜጎቿን ደግሞ በቫይረሱ አጥታለች።