የቻይና መንግስት ታይዋን ወደ ሀገሪቱ የምትቀላቀልበትን ዕቅድ ይፋ አደረገ
የቻይና ፤ ታይዋንን ወደ ሀገሪቱ ለመቀላቀል ሰላም የመጀመሪያ አማራጭ መሆኑን ገልጻች
ቤጅንግ፤ ታይዋን የቻይና አንድ አካል መሆኗ “ጥርት ያለው እውነት ነው” ብላለች
ቤጅንግ፤ ታይዋንን ወደ ቻይና ለመቀላቀል ሰላማዊ አማራጭ የመጀመሪያና ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን አስታወቀች።
የቻይና መንግስት ታይዋን ወደ ሀገሪቱ የምትቀላቀልበትን ዕቅድ ከሰሞኑ ይፋ አድርጓል። በታይዋን ጉዳይ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ሰላም ቅድሚያ የሚሰጠው የመጀመሪያ መፍትሔ እንደሆነም ቻይና አሳውቃለች።
በታይዋን ጉዳይ የተፈጠረው ችግር የሚፈታው የግዛቲቱን ብሎም የሀገሪቱን ሕዝብ ፍላጎት ባሟላ መልኩ እንደሆነም ነው የተገለጸው።
ቤጅንግ በታይዋን ጉዳይ ያዘጋጀችው ሰነድ “የታይዋን ጥያቄ እና ውሕደት በአዲሱ ዘመን” የሚል ርዕስ አለው።
ቤጅንግ በታይዋን ጉዳይ ሰነድ ስታገዘጋጅ ሰሞኑን ይፋ የሆነው “የታይዋን ጥያቄ እና ውሕደት በአዲሱ ዘመን” ሶስተኛዋ ነው።
ከዚህ በፊት ነሐሴ 1993 እንዲሆም መጋት 2000 ላይ ታይዋንን የተመለከቱ ሰነዶች በቻይና በኩል ተዘጋጅተው ነበር።
“የታይዋን ጥያቄ እና ውሕደት በአዲሱ ዘመን” የሚለው ፍኖተ ካርታ በዚህ ወቅት የወጣበት ዋነኛ ምክንያት የታይዋንን ጉይይ አሜሪካ ማጦዟን ተከትሎ እንደሆነም ተገልጿል።
የአሜሪካ ምክር ቤት አፈጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ወደ ታይዋን ማምራታቸውን ተከትሎ በዋሸንግተንና በቤጅንግ መካከል የተካረረ እሰጥ አገባ ተከስቷል።
የዓለም ሀገራትና ዓለም አቀፍ ተቋማት ታይዋን የቻይና አንድ አካል መሆኗን እንደሚያምኑም ከሰሞኑ እየገለጹ ነው።
ቤጅንግ፤ ታይዋን የቻይና አንድ አካል መሆኗ የሚያጋጭ ሀቅ ሳይሆን “ጥርት ያለው እውነት” እንደሆነ አስታውቃለች።
በቻይና መንግስት የተዘጋጀው ሰነድም ታይዋን የቻይና አንድ አካል መሆኗ መቸም የማይፋቅ እንደሆነ በመግቢያው ላይ አስቀምጧል።
ቻይና፤ የአሜሪካ ምክር ቤት አፈጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ወደ ታይዋን ማምራታቸውን ተከትሎ በዋሸንግተንና በቤጅንግ መካከል የነበሩ ወታደራዊና ሌሎች ትብብሮች እንዲሰረዙ ውሳኔ ያስተላለፈች ቢሆንም አሜሪካ ይህንን ተቃውማለች።