ታይዋን፤ ቻይና “የእስያ-ፓሲፊክ ቀጠናን ለመቆጣጠር እየሰራች ነው” አለች
ታይዋን ቻይና “ለወረራ ለመዘጋጀት” የሚያስችላት ወታደራዊ ልምምድ እያደረገች መሆኗን ገለጸች
ጆ ባይደን አሜሪካ ታይዋንን ከቻይና ወረራ ለመጠበቅ “ኃይል ልትጠቀም እንደምትችል” መግለጻቸው ይታወሳል
በአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት የተበሳጨችው ቤጂንግ፤ የጦር አውሮፕላኖቿንና መርከቦቿ በታይዋን ላይ ጥቃት ለመሰንዘር የሚያስችላት ወታደራዊ ልምምድ በማድረግ ላይ መሆናቸው የእየተነገረ ነው፡፡
በዚህ ስጋት የገባቸው የታይዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆሴፍ ዉ ቻይና “ለወረራ ለመዘጋጀት” የሚያስችላት ወታደራዊ ልምምድ እያደረገች መግለጻቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡
ጆሴፍ ዉ፡ የቻይናን የሶሞኑ ወታደራዊ እንቅስቀሴ በማስመልከት በታይፔ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ፤ቤጂንግ በእስያ-ፓሲፊክ አካባቢ ያለውን ሁኔታ ለመቀየር እየሰራች ነውም ብለዋል፡፡
"የቻይና እውነተኛ አላማ በታይዋን የባህር ዳርቻ እና በጠቅላላው አካባቢ ያለውን ሁኔታ መለወጥ ነው"ሲሉም ተናግረዋል፡፡
"ቻይና ልምምዱን እና ወታደራዊ መጫወቻ ደብተሩን ለታይዋን ወረራ ለማዘጋጀት ተጠቅማበታለች” በማለትም ቤጂንግን የከሰሱት ከሰዋል ጆሴፍ ዉ፤በተጨማሪም የታይዋን የህዝብን ሞራል ለማዳከም መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ልምምዶችን እና የሚሳዔል ጥቃቶችን እንዲሁም የሳይበር ጥቃትን፣ የሀሰት መረጃ ዘመቻን እና ኢኮኖሚን የማዳከም ስራ እየሰራች ነው ሲሉም አክለዋል፡፡
የዉ ጋዜጣዊ መግለጫ የመጣው የታይዋን ጦር በደሴቲቱ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመከላከል የራሱን ወታደራዊ ልምምድ ማድረግ ከጀመረ በኋላ መሆኑ ነው።
ጆሴፍ ዉ፡ የቤጂንግ የጦርነት ጨዋታ “የታይዋንን መብት የሚጻረር” እና በታይዋን ዙሪያ ያለውን ውሃ እና ሰፊውን የእስያ-ፓሲፊክ ቀጠናን ለመቆጣጠር የተደረገ ሙከራ ነው”ም ብለውታል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጆሴፍ ዉ፤ የምዕራባውያን አጋሮችን ቻይናን መቃወማቸውንም አመስግነዋል።
"የተቀረው ዓለም አቋም ዴሞክራሲ ለአምባገነንነት ዛቻ እንደማይንበረከክ ለዓለም ግልጽ መልእክት ያስተላለፈ ነው"ም ብለዋል፡፡
ቤጂንግ፤ የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን የሚጎበኙ ከሆነ ጦሯ “ዝም ብሎ እንደማይቀመጥ” ስታስጠነቅቅ መቆየቷ የሚታወስ ነው፡፡
እናም በምስራቅ ታይዋን አከባቢ የተፈጸረው ውጥረት ወዳልተፈለገ የጦር መማዘዝ እንዳያመራ ተሰግቷል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካ፤ ታይዋንን ከቻይና ወረራ ለመጠበቅ ኃይል ልትጠቀም እንደምትችል ፕሬዝዳንት ጆ-ባይደን ከወራት በፊት በጃፓን ጉብኝታቸው መግለጻቸው አይዘነጋም፡፡
ጆ-ባይደን “ቻይና ታይዋንን በተመለከተ ኃይል የምትጠቀም ከሆነ እኛም መጠቀማችን አይቀርም” ነበር ያሉት፡፡