በአሁኑ ወቅት 18 ሀገራት እያንዳንዳቸው ከ2ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኮሮና ተጠቅተውባቸዋል ተባለ
በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረሳ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሚሊዮን ማፉለፉን ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያመለክታል፡፡
በአጠቃላይ በዓለም ዙሪያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት 2,149,818 ህይወታቸውን ሲያጡ የተጠቂዎች ቁጥር 100,032,461 መድረሱን የዩኒቨርሲቲው መረጃ ያመለክታል፡፡ይህ ማለት በአለም ዙሪያ ከ80 ሰዎች አንዱ በኮሮና መያዙን መረጃው ጠቅሷል፡፡
በአሜሪካ በኮሮና ከተጠቁት 25 ሚሊዮን ሰዎች ውስጥ 400ሺ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፣በዚህ ምክንያት አሜሪካ በዓለም ዙሪያ ሩብ የሚሆነውን የተጠቂዎች ቁጥርና 20 በመቶ የሚሆነው የሞት ቁጥር በላይ አስመዝግባለች፡፡
በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ ከ 2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኮሮና የተጠቁባቸው 18 ሀገራት መኖራቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
ከእነዚህም መካከል አውሮፓ ውስጥ ሩሲያ ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ፈረንሳይን ጨምሮ በላቲን አሜሪካ ያሉ አገራት አርጀንቲና እና ብራዚልን እንዲሁም ኢሲያዊቷ ህንድ ትገኝበታለች፡፡
በተጨማሪም ህንድ ፣ ሜክሲኮ ፣ ብሪታንያ ፣ ጣሊያን እና ፈረንሳይን ጨምሮ ከ 50 ሺህ በላይ ሰዎች የሞቱባቸው 12 ሀገራት ናቸው፡፡
በብሪታንያ በተከሰተው ወረርሽኝ ከ 100,000 በላይ ሰዎች በሚሞቱበት ጊዜ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በዚህ አስከፊ ስታትስቲክስ ውስጥ የተካተተውን ሀዘን ለማስላት ከባድ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በ2012ዓ.ም ታህሳስ ወር በቻይና ሁቤ ግዛት የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ መላውን አለም በማዳረስ የፖለቲካና ማህበራዊ ቀውስን አስከትሏል፡፡