ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዶክ የቤን አምር ጎሳ አባል የሆነውን የከሰላ ግዛት መሪ ከስልጣን ማንሳታቸው ተቃውሞ አስከትሏል
ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዶክ የቤን አምር ጎሳ አባል የሆነውን የከሰላ ግዛት መሪ ከስልጣን ማንሳታቸው ተቃውሞ አስከትሏል
በሱዳን ምስራቃዊ ግዛት ከሰላ ከጎሳ ጋር የተያያዘውን ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ በተፈጠረ ግጭት ሰዎች መሞታቸውንና መቁሰላቸውን የሀገሪቱ የዜና አገልግሎት ሱና ዘግቧል፡፡
ለተቃውሞው መነሻ ሆነው የከሰላ መሪ የነበረው ሳሌህ አማር ለምን ተነሳ በማለት የእሱ ጎሳ አባላት ማለትም የቤን አምር ብሄር አባላት ናቸው ተቃውሞ ያስነሱት፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ባለፈው ማክሰኞ የቤን አምር ጎሳ አባል የሆነውን ሳሌህን ከስልጣን ማንሳታቸውን ተቃውሞ አስከትሏል፡፡
እንደ ሱና ዘገባ ሰላማዊ ሰልፉ ከከሰላ ግዛት ፍቃድ ማግኘቱን የገለጸ ሲሆን ችግሩ የተፈጠረው የተወሰኑት ሰልፈኖቹ ተቃውሟቸውን በፍሪደም አደባባይ ካሰሙ በኋላ የጋሽ ድልድይን ለመዝጋት ሲንቀሳቀሱ ነው ብሏል፡፡
የሟቾችን ቁጥር በተመለከተ ዘገባው ያለው ነገር የለም፤ ነገርግን ቢቢሲ የህክምና ዶክተሮችን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ስድስት ሰዎች መሞታቸውን ዘግቧል፡፡
የቤን አምር ጎሳ ስልጣን መያዝ ከወራት በፊት በሌሎች ጎሳዎች ተቃውሞ ተፈጥሮ የሰው ህይወት መጥፋቱ ይታወሳል፡፡