ጀርመናዊን ከከተማ ወደ ገጠር እየፈለሱ እንደሆነ ተገለጸ
ፍልሰቱን ተከትሎ በከተሞች የሰራተኛ እጥረት እንዳያጋጥም ተሰግቷል
ጀርመናዊያን ግርግር እና ኑሮ ውድነት የበዛበት የከተማ ህይወትን በመጥላት ወደ ገጠር አካባቢዎች መሄድን እየመረጡ ነው ተብሏል
ጀርመናዊን ከከተማ ወደ ገጠር እየፈለሱ እንደሆነ ተገለጸ፡፡
በአውሮፓ የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችው ጀርመን ከከተሞች ወደ ገጠር አካባቢዎች በመሄድ የሚኖሩ ዜጎቿ ቁጥር እየጨመረ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ከዚህ በፊት ጀርመንን ጨምሮ በመላው ዓለም ያለው ዕውነት ከገጠር አካባቢዎች ወደ ከተሞች የሚፈልሱ ሰዎች ቁጥር በመብዛቱ ከተሞች ሲጨናነቁ ይታይ ነበር፡፡
በተለይም በርሊን ሙኒክ እና ላይፕዚሽ ከተሞች ከገጠር በሚፈልሱ ጀርመናዊያን የተጨናነቁ ከተሞች የነበሩ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የተገላቢጦሽ እየሆነ ነው ተብሏል፡፡
በጀርመን ኑሯቸውን ከከተማ ይልቅ ወደ ገጠር በመሄድ የሚያመቻቹ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ከፈረንጆቹ 2017 ጀምሮ እድሜያቸው ከ30-49 የሆናቸው ጀርመናዊያን ቤተሰቦቻቸውን በመያዝ ወገ ገጠራማ ስፍራዎች እየፈለሱ እና ኑሯቸውን በዚያ እያደረጉ እንደሆነ የጀርመን ደምጽ ዘግቧል፡፡
ጀርመን በሀገሯ ከሶስት ዓመት በላይ ለኖሩ ዜጎች ዜግነት ልትሰጥ ነው
የበርሊን ስነ ህዝብ ልማት ኢንስቲትዩት ባስጠናው ጥናት ገጠራማ አካባቢዎች ባለ ህይወት የሚሳቡ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ እንደሆነ አስታውቋል፡፡
በገጠራማ አካባቢዎች ንጹህ አየር መኖሩ፣ ተፈጥሯዊ ቦታዎች እንደልብ መገኘት፣ በከተሞች ያለው የኑሮ ውድነት እየጨመረ መሄድ እና ግርግር የበዛበት ህይወትን መጥላት ለፍልሰቱ በምክንያትነት ተቀምጠዋል፡፡
በሀገሪቱ የገጠራማ አካባቢ ከዚህ በፊት የነበሩ በቂ መዝናኛ አለመኖር፣ የኢንተርኔት አገልግሎት መቆራረጥ እና የሕጻናት መዝናኛ ስፍራዎች አለመኖር ችግሮች እየተፈቱ መሄዳቸው ጀርመናዊያን አይናቸውን ወደ ገጠር አካባቢዎች እንዲያደርጉ እያደረገ ነውም ተብሏል፡፡
የኮሮና ቫይረስ መከሰት ደግሞ የከተሞች ህይወትን መልኩን እንዲቀይር ካደረጉ ተጨማሪ ምክንያቶች መካከል አንዱ እንደሆነ ሲገለጽ ገጠራማ አካባቢዎች ነዋሪ አልባ እንዳይሆኑ የተለያዩ ማበረታቻዎች መሰጠት መጀመራቸውም ሌላኛው ገፊ ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል፡፡