በሻምፒዮንስ ሊጉ ካርሎ አንቸሎቴ እና ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ከ100 ጊዜ በላይ አሸንፈዋል
የማንቸስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ትናንት ምሽት በኢትሃድ አዲስ ሪከርድ አስመዝግበዋል።
ቡድናቸው ሪያል ማድሪድን አሸንፎ ለፍጻሜ ሲደርስ 100ኛ ድላቸው ሆኖ ተመዝግቦላቸዋል።
ለሶስት ዋንጫ እየተፋለሙ የሚገኙት የ52 አመቱ አሰልጣኝ በባየር ሙኒክ፣ ባርሴሎና እና ማንቸስተር ሲቲ ቆይታቸው በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አራት ጊዜ ለፍጻሜ ደርሰዋል።
በተጫዋችነት ዘመናቸው አንድ ጊዜ በአሰልጣኝነት ደግሞ ሁለት ጊዜ ከባርሴሎና ጋር ዋንጫውን አንስትዋል። ጋርዲዮላ ሻምፒዮንስ ሊግን በተጫዋችነት እና አሰልጣኝነት ካነሱ ሰባት ኮከቦች ውስጥ አንዱ ናቸው።