“በ8 ዓመታት ውስጥ እንደዚህ አይነት ጊዜ አሳልፈን አናውቅም”- ጋርዲዮላ
አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ “4ለ0 ስትሸነፍ ብዙ ማውራት አይጠበቅብህም” ብለዋል
ቡድናቸው ተከታታይ 5ኛ ጨዋታ የተሸነፈው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ “እውነታውን ተቀብለን ይህን መስበር አለብን” ብለዋል
የማንችስተር ሲቲ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቡድናቸው ተከታታይ 5ኛ ጨዋታ መሸነፉን ተከትሎ በሰጡት አስተያየት “በ8 ዓመታት ውስጥ እንደዚህ አይነት ጊዜ አሳልፈን አናውቅም” ብለዋል።
አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቡድናቸው ማንቸስተር ሲቲ በሜዳው በቶትንሃም 4ለ0 ሽንፈት ከገጠመው በኋላ በሰጡት አስተያየት ነው ይህንን ያሉት።
ጋርዲዮላ በንግግራቸውም፤ “እውነታውን ተቀብለን ይህንን ለመቀየር መስራት ይጠበቅብናል ማለታቸው ነው” የተሰማው።
አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የድህረ ጨዋታ አስተያየታቸውን ሲሰጡ፤ “4ለ0 ስትሸነፍ ብዙ ማውራት አይጠበቅብህም” ብለዋል።
ቶትንሃ ሆትስፐርስ ማንቸስተር ሲቲን በሜዳው 4ለ0 በማሸነፋቸውም የእንኳን ደስ አላችሁ መልክት አስተላልፈዋል።
አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በንግግራቸው አክለውም፤ “ተከታታይ ጨዋታዎች መሸነፍ አለመደብንም ነገርግን ተፈጥሯል፤ ይህንን ሁኔታ ለመቀየር የምንችለውን ሁሉ ማድረግ አለብን” ብለዋል።
"በስምንት አመታት ውስጥ እንደዚህ አይነት ኑሮ አልኖርንም፤ ይዋል ይደር እንጂ ካለንበት አቋማችን መውረዳችን እንደማይቀር ተሰምቶኝ ነበር፤ ይሁን እንጂ ሶስት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን በተከታታይ እንሸንፋለን ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር” ብለዋል አሰልጣኙ።
“አንዳንድ ጊዜ በእግር ኳስ ውስጥ የሚከሰት እውነታ መካድ አንችልም፤ ነገርግን በሚያስደንቅ ሁኔታ ከዚህ ሁኔታ እንወጣለን” ብለዋል።
ጋርዲዮላ በተጫዋቾቹ ላይ ያለው እምነት አሁንም አልተናወጠም የተባለ ሲሆን፤ ክለቡ ያለበትን ሁኔታ ለመቀየር እንደሚሰሩ መናገራቸውም ነው የተገለጸው።
በትናትናው እለት በተካሄደው በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ በሜዳው ከቶተንሀም ጋር ያደረገውንጨዋታ 4ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት መሸነፉ ይታወቃል።
ይህንን ተከትሎ ማንቸስተር ሲቲ በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ እየተመራ በ2024 የውድድር ዘመን ሶስት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን ጨምሮ አምስተኛ ተከታታይ ሽንፈቱን አስተናግዷል።
በቀጣይ ሳምንት እሁድ በሚደረግ 13ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ሊቨርፑል ከማንችስተር ሲቲ የሚጨወቱ ሲሆን፤ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ “ በተለይ ቀጣዩን የሊቨርፑል ጨዋታ ማሸነፍ አለብን “ ብለዋል።
የዘንድሮ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ደረጃ ሰንጠረዥን ሊቨርፑል በ28 ነጥብ ሲመራ፤ ማንቸስተር ሲሊ በ23 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።