ስለ ተጠባቂው ማንችስተር ሲቲ እና አርሰናል እግር ኳስ ጨዋታ አዳዲስ መረጃዎች
ለዋንጫ በሚደረገው ፉክክር ላይ ተጽዕኖ የሚኖረው ይህ ጨዋታ ዛሬ ምሽት 12፡30 ላይ በኢትሀድ ይካሄዳል
በኢትሀድ የተደረጉ ያለፉት ስምንት ጨዋታዎችን ማሸነፍ ያልቻለው አርሰናል ዛሬ ድል ከቀናው አዲስ ታሪክ ያስመዘግባል
ስለ ተጠባቂው ማንችስተር ሲቲ እና አርሰናል እግር ኳስ ጨዋታ አዳዲስ መረጃዎች
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 30ኛ ሳምንት ዛሬም ቀጥለው የሚካሄዱ ሲሆን ምሽት 13፡30 ላይ የሊጉ መሪ አርሰናል ከማንችስተር ሲቲ በኢትሀድ ስታዲየም ይጫወታሉ፡፡
ይህ ጨዋታ ሁለቱም ክለቦች የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ከፍተኛ ትንቅንቅ ላይ በመሆናቸው ጨዋታውን የበለጠ አጓጊ እና ተጠባቂ አድርጎታል፡፡
በዚህ ጨዋታ ላይ ማንችስተር ሲቲዎቹ ጆን ስቶንስ እና ካይል ወከር በጉዳት አለመሰለፋቸው የተረጋገጠ ሲሆን ማኑኤል ኢካንጂ፣ ኬቪን ደብሮይኒ እና ማቲያስ ኑኔዝ ደግሞ ከጉዳታቸው አገግመው የመሰለፍ እድላቸው ከፍተኛ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
እንዲሁም ግብ ጠባቂው ኤደርሰን ደግሞ ከጡንቻ ጉዳቱ አገግሞ ሊሰለፍ ይችላልም ተብሏል፡፡
በአርሰናል በኩል ደግሞ ጋብርኤል፣ ሳካ እና ማርቲኔሊ የመሰለፍ እድላቸው ከፍተኛ እንደሆነ ሲገለጽ ግብ ጠባቂው ራያ ከብሬንትፎርድ ጨዋታ በኋላ ዳግም ወደ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ይመለሳል፡፡
በእግር ኳስ ጨዋታ አዲስ የተዋወቀው ሰማያዊ ካርድ ምንድን ነው?
ማንችስተር ሲቲ ባለፉት ስምንት ጊዜ በሜዳው ከአርሰናል ጋር ያደረጋቸውን ተከታታይ ጨዋታዎች ያልተሸነፈ ሲሆን ባሳለፍነው ጥቅምት ወር ላይ በኢምሬት ስታዲየም ያደረገውን ጨዋታ በአርሰናል ተሸንፎ ነበር፡፡
ሲቲ በሜዳው የተሸለ ያለመሸነፍ ታሪክ ያለው ሲሆን ካደረጋቸው 38 ጨዋታዎች 33ቱን ሲያሸንፍ በአምስቱ አቻ ወጥቷል፡፡
ይሁንና ማንችስተር ሲቲ ከትላልቅ ቡድኖች ጋር ሲገናኝ ጥሩ የማሸነፍ ልምድ የሌለው ሲሆን በተለይም ከቶፕ አምስት ቡድኖች ጋር ካደረጋቸው ጨዋታዎች ውስጥ በሁለቱ ሲሸነፍ በሶስቱ ደግሞ ነጥብ ለመጣል ተገዷል፡፡
የሲቲው አጥቂ አርሊንግ ሀላንድ ከተሰለፈባቸው 16 ጨዋታዎች ውስጥ በ11ዱ ጎል ሳያስቆጥር ቀርቷል፡፡
አርሰናል ደግሞ ባለፉት ያደረጋቸውን ስምንት ጨዋታዎች ሁሉንም ማሸነፍ የቻለ ሲሆን 33 ጎል በማስቆጠር ጥሩ የማሸነፍ ወኔ ይዞ ወደ ኢትሀድ ተጉዟል፡፡
አሁን ያለው የሚካኤል አርቴታ ቡድን ያስቆጠራቸው ጎሎች ብዛት ከ20 ዓመት በፊት ከነበረው የአርሰን ቪንገር ቡድን የማይገበሩት ከሚባለው ስብስብ ጋር አቻ ለመሆን አንድ ጎል ብቻ ይቀረዋል፡፡
ጀርመናዊው ካይ ሀቨርትዝ ዛሬ ጎል ካስቆጠረ በቴሪ ሄነሪ የተያዘውን በአምስት ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ጎል የማስቆጠር ታሪክን ይጋራል፡፡