ለጠበቃ በሰዓት 5 ሺህ ዩሮ ክፍያ የሚፈጸምበት የማንችስተር ሲቲ እና የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክርክር ችሎት
ማንችስተር ሲቲ 115 የህግ ጥሰት ፈጽሟል በሚል ክስ ተመስርቶበታል
የክስ ሒደቱ የፊታችን የካቲት ላይ የመጨረሻ ፍርድ ያገኛል ተብሏል
በሰዓት 5 ሺህ ዩሮ ክፍያ የሚፈጸምበት የማንችስተር ሲቲ እና የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክርክር ችሎት
የእንግሊዙ ማንችስተር ሲቲ እግር ኳስ ክለብ የሊግ አወዳዳሪ ተቋም ያስቀመጠውን የገንዘብ ስርዓት ጥሷል በሚል 115 ክሶች ቀርቦበታል፡፡
የአምናው የፕሪሚየር ሊጉ እና አውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊው ማንችስተር ሲቲ የህግ ጥሰት እንዳልፈጸመ የገለጸ ቢሆንም ጉዳዩ ወደ ክርክር አምርቷል፡፡
ክለቡ ከፈረንጆቹ 2009 እስከ 2018 ባሉት 11 ዓመታት ውስጥ የሊጉን የእግር ኳስ የገንዘብ አሰራር ስርዓት ጥሷል የሚል ክስ የቀረበበት ሲሆን ህጉን እንዳልጣሰ ማረጋገጫ እንዲያመጣ ታዟል፡፡
ይህን ተከትሎ 10 ሳምንት ይፈጃል የተባለው የማንችስተር ሲቲ እና የፕሪሚየር ሊጉ የሕግ ክርክር ትናንት በለንደን ተጀምሯል፡፡
ከአውሮፓ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ በፊት የእንግሊዝን አሸናፊነት የሚገልጽ ንቅሳት የተነቀሰው እንግሊዛዊ
ባለፉት 11 ዓመታት ውስጥ ስምንት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን፣ አንድ ቻምፒዮንስ ሊግ እና ሌሎች ዋጫዎችን ያሸነፈው ማንችስተር ሲቲ በዓለም ላይ አለ የተባለ ጠበቃ ቀጥሯል፡፡
ሎርድ ፓኒክ የተሰኘው የእንግሊዝ ታዋቂ ጠበቃ ደግሞ ማንችስተር ሲቲ የቀጠረው ጠበቃ ሲሆን ይህ የሕግ ባለሙያ ከዚህ በፊት ከንግስት ኤልሳቤት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ጀምሮ ለበርካታ ዜጎች በጠበቃነት አገልግሏል፡፡
ማንችስተር ሲቲ ለዚህ ዝነኛ ጠበቃ በሰዓት 5 ሺህ ዩሮ ለመክፈል የተስማማ ሲሆን ይህ ጠበቃ ከዚህ በፊት ማንችስተር በአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ተላልፎበት የነበረውን እገዳ ይግባኝ በመጠየቅ ክለቡን ነጻ አስብሏል፡፡
በማንችስተር ሲቲ ክለብ ደጋፊዎች ሳይቀር የሚዘመርለት ይህ ጠበቃ አሁን የተያዘው ክርክር ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚያመራ ከሆነ ክፍያው እየጨመረ እንደሚሄድ መስማማታቸው ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የሁለቱ ወገኖች የህግ ክርክር የመጨረሻ ውሳኔ የፊታችን የካቲት ወር መጨረሻ ቀናት ላይ እንደሚተላለፍ ይጠበቃል፡፡
የማንችስተር ሲቲ አሰልጣኝ ፔፔ ጋርዲዮላ ከሰሞኑ በሰጡት አስተያየት “ሁሉም እኛ እንድንቀጣ ይፈልጋል” ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
ማንችስተር ሲቲ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ የነጥብ ቅነሳን ጨምሮ ሌሎች ቅጣቶች ሊጣሉበት እንደሚችሉ ይጠበቃል፡፡