እየተጠናቀቀ ባለው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ ዝውውሮች ምን ምን ናቸው?
በቸልሲ አልፈልግህም የተባለው ስተርሊንግ፣ የአርሰናሉ ራምሳዴል እና ኔኪታህ፣ ሉካ ቶኒ እና ሌሎችም ዝውውሮች ዛሬ አልያም ነገ ይጠናቀቃሉ
ቸልሲ፣ አርሰናል፣ ማንችስተር ዩናይትድ እና ኒውካስትል ተጠባቂ ዝውውሮች ይፈጽማሉ ተብለው ከሚጠበቁ ክለቦች መካከል ዋነኞቹ ናቸው
እየተጠናቀቀ ባለው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ ዝውውሮች ምን ምን ናቸው?
ከሁለት ሳምንት በፊት የተጀመረው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የተጫዋች ዝውውር ጊዜ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውታል።
በቀጣዮቹ ቀናት ይፈጸማሉ ተብለው ከሚጠበቁ ዝውውሮች መካከል በቸልሲ እንደማይፈለግ የተነገረው ራሂም ስተርሊግ ዝውውር ዋነኛው ነው።
ስተርሊንግ ወደ አስተን ቪላ አልያም ክሪስታል ፓላስ እንደሚዘዋወር ይጠበቃል።
ሌላኛው ይፈጸማል ተብሎ የሚጠበቀው ዝውውር የማንችስተሩ ማክቶሚናይ እና ጄዳን ሳንቾ ዝውውር ነው።
ከአሰልጣኝ ቴን ሀግ ጋር ግጭት ውስጥ የነበረው ሳንቾ ወደ ባርሴሎና አልያም ጁቬንቱስ እንደሚያቀና ይጠበቃል።
ማክቶሚናይ ደግሞ የጣልያኑን ናፖሊ እንደሚቀላቀል ተገልጿል።
በመጭዎቹ ጥቂት ቀናት በዝውውር ጉዳይ ስራ ይበዛባቸዋል ተብሎ ከሚጠበቁ ክለቦች መካከል ቸልሲ እና አርሰናል ተጠቃሽ ናቸው።
ቸልሲ ሮሚዮ ሉካኩ፣ ቤን ችል ዌል፣ ቻሎባህ እና ሌሎችም ተጫዋቾች ወደ ተለያዩ ክለቦች እንደሚያመሩ ይጠበቃል።
አርሰናል በበኩሉ ግብ ጣባቂው አሮን ራምሳደል፣ ኤዲ ኔኪታህ እና ሌሎችም ተጫዋቾች ክለቡን ለቀው በሽያጭ እና ውሰት እንደሚያመሩ እየተገለጸ ይገኛል።
የብሬንት ፎርዱ ኢቫን ቶኒ ወደ አርሰናል አልያም ቸልሲ ክለቦች እንደሚያመራ ቢቢሲ ዘግቧል።
ኬራን ትሪፐር፣ ጃኦ ካንሴሎ፣ ማርክ ጉሂ እና ሌሎችም ተጫዋቾች ወደ አዲስ ክለብ እንደሚያመሩ እየተገለጸ ይገኛል።