ሩሲያዊው ተዋናይ በደረሰበት አደጋ መድረክ ላይ ህይወቱ አለፈ
ተዋናዩ በሞስኮው ቦሎሺ ቴአትር ቤት ትወና በማቅረብ ላይ እያለ ነው ህይወቱ ያለፈው
ተመልካቾች ተዋናዩ በሚወድቅበት ጊዜ የቴአትሩ አካል መስሏቸው በመከታተል ላይ እንደነበሩ ተነግሯል
ሩሲያዊው አርቲስት የቴአትር ትወና በማቅረብ ላይ እያለ በደረሰበት አደጋ መድረክ ላይ ሕይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።
ያቬንጊ ኩሌሽ የተባለው ሩሲያዊው አርቲስት በትናትናው እለት “ሳድኮ” የተባለ የኦፔራ ትርኢት በማቅረብ ላይ እያለ በደረሰበት አደጋ ህይወቱ ማፉም ተነግሯል።
አደጋው ቦሎሺ በተባለው የሞስኮ ታዋቂ ቴአትር ቤት ውስጥ ማጋጠሙ የተነገረ ሲሆን፤ መድረኩን ለማስዋብ የተቀመጠ ቁስ በአርቲስቱ ላይ በመውደቁ ነው አደጋው የተከሰተው።
አደጋውን ተከትሎ የተለቀቁ ተንቀሳቃሽ ምስሎች አንደሚያሳዩት ከሆነ የአርቲስቱን ሕይወት ለመታደግ ብዙ ሙከራዎች ቢደረጉም ሊሳኩ አልቻሉም።
የ37 ዓመቱ አርቲስት ያቬንጊ ኩሌሽ ሞትን ተከትሎ አደጋው እንዴት ሊከሰት ቻለ የሚለውን ለማጣራት ምርመራ መጀመሩም ነው የተነገረው።
አደጋውን ተከትሎ ቦሎሺ ቴአትር ቤት ትናንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ፤ ቴአትሩ ወዲያውኑ እንዲቋረጥ ተደርጎ ተመልካቾችም ከአዳራሽ እንዲወጡ መደረጉን ያመላክታል።
ያቬንጊ ኩሌሽ የተባለው አርቲስት በተሳሳተ አቅጣቻጫ በመሄዱ ለመድረክ ማሰዋቢያ የተቀመጠው ከባድ ቁስ ሳይወድቅበት አይቀርም ብሏለ ቴአትር ቤቱ በመግለጫው።
በሁኔታው የተደናገጡ ተመልካቾች በመጀመሪያ ሁኔታው ቴአትሩ አካል መስሏቸው ሲከታተሉት እንደነበረ በማበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባጋሩት ጽህፉ ገልጸዋል።
ሆኖም ግን ከመድረኩ ላይ አንድ ሰው “ብዙ ደም ፈሷል አምቡላንስ ጥሩ” ብሎ ሲጮህ አደጋ እንደሆነ እንደተረዱ እና ሁኔታው በጣም አስደንጋጭ እንደነበረም ጠቅሰዋል።
ያቬንጊ ኩሌሽ የተባለው አርቲስት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2002 ጀምሮ ቦሎሺ ትአትር ቤት ውስጥ በትወና ሙያ ሲያገለግል እንደነበረ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃ መረጃ ያመለክታል።