የልጃቸውን ስም “ቭላድሚር ፑቲን” ብለው የሰየሙት ስዊድናውያን ጥንዶች ክልከላ ደረሰባቸው
‘ስካቴቨርክት’ የተባለው የስዊድኑ ታክስ ኤጀንሲ ስሙን ለምን ውድቅ እንዳደረግ እስካሁን ማብራሪያ አልሰጠም
በስዊድን ህግ መሰረት ወላጆች ለልጆቻው የሚያወጡት ስም አደጋ የሚያሰከትል፣ አጸያፊና ችግር ፈጣሪ ለሆን አይገባም
የልጃቸውን ስም በሩሲያው ፕሬዝዳንት “ቭላድሚር ፑቲን” ብለው የሰየሙት ስዊድናውያን ጥንዶች ስሙን መጠቀም አትችሉም መባላቸው ተሰምቷል።
ስሙን ውድቅ ያደረገው የስዊድኑ ታክስ ኤጀንሲ መሆኑንም የስዊድን ፐብሊክ ሬዲዮ ብሮድካስተርን ጠቅሶ ኦዲቲ ሴንትራል በድረ ገጹ አስነብቧል።
“ቭላድሚር ፑቲን” የሚለውን ስም እንዳይጠቀሙ በታክስ ኤጀንሲው የተከለከሉት ጥንዶች በስዊድኗ ላሆም ከተማ ነዋሪ መሆናቸውም ታውቋል።
‘ስካቴቨርክት’ የተባለው የስዊድኑ ታክስ ኤጀንሲ ስሙን ለምን ውድቅ እንዳደረግ እስካሁን ማበራሪያ እንዳልሰጠ ተነግሯል።
- ወንዶችና ሴቶች የተለያየ ቋንቋ የሚናገሩባት የናይጄሪያዋ ‘ኡባንግ’ መንደር
- ታሊባንን ሽሽት ወደ እንግሊዝ በመጓዝ ላይ የነበረች መንገደኛ በአውሮፕላን ውስጥ ወለደች
ሆኖም ግን በስዊድን ህግ መሰረት ወላጆች ለልጆቻው የሚያወጡት ስም አደጋ የሚያሰከትል፣ አጸያፊ እና ችግር ፈጣሪ ለሆን አይገባም ሲል የደነግጋል።
በዚህም መሰረት “ቭላድሚር ፑቲን” የሚለው ስም ከሀገሪቱ ህግ አኳያ በየትኛው ጎራ ስር ሊመደብ ይችላል የሚለው እስካሁን በግልጽ አልተጠቀሰም።
በስዊድን በአውሮፓውያኑ በ1982 በወጣው እና በ2017 በተሸሻለው ህግ መሰረት ወላጆች ለልጆቻው የሚያወጡትን ስም ልጁ ከተወለደ በ3 ወራ ውስጥ ‘ስካቴቨርክት’ ለተባለው የስዊድኑ ታክስ ኤጀንሲ ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል።
በዚህም መሰረት ተቋሙ ባለፉት ዓመታት በርካታ ስሞችን ውድቅ አድርጓል የተባለ ሲሆን፤ ውድቅ ከተደረጉ ስሞች ውስጥም “ፎርድ፣ ፒልዝነር፣ ኪው እና አላህ” የሚባሊ ይገኙበታል።
በተቃራኒው ጎግል፣ ማቴሊካ እና መሰል ወጣ ያሉ ስሞችን ተቀብሎ ማጽደቁን ዘገባው አመልክቷል።