ፕሬዘዳንት ኪር በአንድ ወቅት የአማፂ መሪ የነበሩትን ማቻርን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንት አድርገው ሾሙ
ፕሬዘዳንት ኪር የአማፂ መሪ የነበሩትን ማቻርን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንት አድርገው ሾሙ
የደቡብ ሱዳን ፕሬዘዳንት ሳልቫ ኪር በአንድ ወቅት የአማፂ መሪ የነበሩትን ሪክ ማቻርን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንት አድርገው መሾማቸው የተገለጸ ሲሆን ይህም ዛሬ ይመሰረታል ተባለውን የሀገሪቱን የአንድነት መንግስት ለመመስረት አንድ እርማጃ ወፊት መሆኑ ተነግሯል፡፡
ፕሬዘዳንቱ ከዚህ በተጨማሪም ማዳም ርብቃ ኒያንዴንግ ዲ ማቢዎርን በምክትል ፕሬዘዳንትንት በመሾም፣ የመጀመሪያዋ ሴት ምክትል ፕሬዘዳነት እንዲሆኑ አስችሏቸዋል፡፡ ጀምስ ታባን ዋኒ ኢጋ እና ታባን ዴንግ ጋይም ምክትል ፕሬዘዳንት ሆነው ተሾመዋል፡፡
ፕሬዘዳንት ሳልቫ ኪር ከዚህ በፊት የጸጥታ ጉዳይ አማካሪ የሆኑትን ቱት ኬው ጋትሉአክና የፕሬዘዳንታዊ ጉዳይዮች ሚኒስትር የነበሩትን ማይክ አይ ዴንግን በድጋሚ ሾመዋቸዋል፡፡
ደቡብ ሱዳን ከሱድን ተገንጥላ እ.ኤ.አ በ2011 ሀገር ከሆነች በኋላ ለአምስት አመታት የቆየ የእርስበእርስ ጦርነት ተቀስቅሶ ምናልባትም ከሩዋንዳ የዘርማጥፋት በኋላ አስከፊ የሚባል ስደተኞችን ቁጥር መፍጠሯ ይታወሳል፡፡
በአሜሪካና በተባበሩት መንግስተት ድርጅት ጫና ምክንያት ኪርና ማቻር እ.ኤ.ኤ. በ2018 የሰላም ስምምነት ፈርምው ነበር፡፡