ከ90 ሚሊየን በላይ የኦርቶድክስ እምነት ተከታዮች ያሏት ሩሲያ የጥምቀት በዓልን በድምቀት ከሚያከብሩ ሀገራት መካከል ነች
ኢየሱስ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ የተጠመቀበትን ዕለት በማሰብ የሚከበረው የጥምቀት በዓል በተለያዩ የአለም ሀገራት በሚገኙ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ከሚከበሩ ዓመታዊ በዓሎች አንዱ ነው።
ከ90 ሚሊየን በላይ የኦርቶድክስ እምነት ተከታዮች ያሏት ሩሲያም የጥምቀት በዓልን በድምቀት ከሚያከብሩ ሀገራ መካከል ተጠቃሽ ነች።
የሩሲያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የእየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ መጠመቅን እና ሶስቱ ስላሴዎችን ለማስታወስ በበረዶ ውሃ ውስጥ ራሳቸውን ሶስት ጊዜ ይነከራሉ።
የሩሲያ ኦርቶዶክሳዊያን ለሶስት ጊዜያት ራሳቸውን በበረዶ ውሃ ውስጥ መንከር ሀጢያታቸውን ያነፃል ብለው ያምናሉ።
የእምነቱ ተከታዮች በጥምቀት ወቅት ሁሉም ውሃ የተቀደሰ መሆኑን የሚያምኑ ሲሆን፥ በረዶውም ጤናቸው ላይ በጎ ተፅዕኖ እንዳለውም ያምናሉ።
ምንጭ:- በኢትዮጵያ የሩሲያ ኢምባሲ