አልጀሪያ የቻይናውን ሲኖፋርም የኮሮና ቫይረስ ክትባት ልታመርት ነው
አገሪቱ እስከ መጭው ታህሳስ ድረስም የሩሲያውን ስፑትኒክ ክትባት የማምረት እቅድ አለኝም ብላለች
አልጀሪያ ከአንድ ወር በኋላ 1 ሚሊዮን ዶዝ ሲኖፋርም ክትባትን አመርታለሁ ብላለች
አልጀሪያ የቻይናውን ሲኖፋርም የኮሮና ቫይረስ ክትባት ማምረት ልትጀምር ነው።
ሰሜን አፍሪካዊቷ አገር አልጀሪያ በኮሮና ቫይረስ ክፉኛ ከተጠቁ አገራት መካከል አንዷ ስትሆን ከጠቅላላ ህዝቧ 70 በመቶውን ማለትም 45 ሚሊዮን ዜጎቿን የመከተብ እቅድ እንዳላት ገልጻለች።
ለአልጀርሱ ስምምነት መፈረም አስተዋጽኦ ያደረጉት የቀድሞው የአልጀሪያ ፕሬዝዳንት አረፉ
ሮይተርስ የአገሪቱን ጤና ሚኒስቴር ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ሲኖፋርም የተሰኘውን የቻይናውን የኮሮና ቫይረስ ክትባት በአገር ውስጥ ማምረት ትጀምራለች።
በጥቅምት ወር 1 ሚሊዮን፤ ህዳር ላይ ሁለት ሚሊዮን እንዲሁም በታህሳስ ወር ላይ ደግሞ 3 ሚሊዮን ዶዝ የኮሮና ቫይረስ እንደምታመርት አገሪቱ አስታውቃለች።
ክትባቱ የሚመረተው በአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል በሚገኘው ሴዳል በተሰኘው መንግስታዊ የመድሀኒት ማምረቻ ፋብሪካ ውስጥ ነው ተብሏል።
ኢትዮጵያ በአልጀርስ የሚገኘውን ኢምባሲዋን እንደምትዘጋ አስታወቀች
አገሪቱ ክትባቱን የምታመርተው ከቻይና መንግስት ጋር በተደረገ ስምምነት መሰረት ሲሆን በቀጣዩ ዓመት ላይ ደግሞ የሩሲያውን ስፑትኒክ የተሰኘውን የኮሮና ቫይረስ ክትባት ማምረት እንደምትጀምር ገልጻለች።
ከፈረንጆቹ 2022 ዓመት በኋላም በወር 5 ሚሊዮን ዶዝ የኮሮና ቫይረስ ክትባት የማምረት ግብ ማስቀመጧንም ዘገባው አክሏል።
የሁለቱን አገራት የኮሮና ቫይረስ ክትባት ካመረተች እና 45 ሚሊዮን ዜጎቿን ከከተበች በኋላ ወደ ሌሎች የአፍሪካ አገራት የመሸጥ እቅድ እንዳላትም አልጀሪያ አስታውቃለች።