በማብረር ላይ እያሉ ለ28 ደቂቃ ያክል እንቅልፍ የወሰዳቸው አብራሪና ረዳት አብራሪ
አብራሪዎቹ በተኙበት ሰዓት አውሮፕላኑ የከበረራ መስመሩ ለቆ ወጥቶ ነበር
የባቲክ ኤር አውሮፕላን 153 መንገደኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ ነበረ
በኢንዶኔዥያ የሚገኘው የባቲክ ኤር አውሮፕላን አብራሪውና ረዳት አብራሪው በበረራ ላይ እያሉ ለግማሽ ሰዓት ያህል እንቅልፍ ጥሏቸው ከበረራ መስመራቸው ወጥተው ነበር ተባለ።
ክስተቱ ያጋጠመው ባሳለፍነው ጥር ወር ላይ ነው የተባለ ሲሆን፤ ሁለቱም አብራሪዎች በማንቀላፋታቸው ምክንያት የ153 መንገደኞች ህይወት አደጋ ላይ ወድቆ እንደነበረም ተነግሯል።
በአውሮፕላኑ በወቅቱ በደቡብ ምስራቅ ኢንዶኔዢያ ከምትገኘው ሱላዌስቲ ወደ ዋና ከተማዋ ጃካርታ በመብረር ላይ ነበረ።
ከበረራው ቀድም ብሎ በነበረው ምሽት ላይ አንደኛው አብራሪ በቂ እረፍት እንዳላደረገም ተነግሯል።
በበረራው እለት አውሮፕላኑ መብረር ከጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ዋና አብራሪው ረዳት እባሪውን ማረፍ እንደሚፈልግ ነግሮት ያስፈቅደውና ሙሉ የበረራውን ኃላፊነት ይሰጠዋል።
ኃፊነት የተቀበለው ረዳት እባበሪው ግን በዙም ሳይቆይ እንቅልፍ እንደወሰደው ነው የተገለጸው።
በረዳት አብራሪው የመጨረሻ መልእክት ከተላለፈ ደቂቃዎች በኋላ በጃካርታ የሚገኙ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ከአውሮፕላኑ አብራሪዎች ጋር ለመገናኘት ያደረጉት ሙከራም ሳይሳካ ይቀራል።
የመጨረሻ መልእክት ከተመዘገበ ከ28 ደቂቃዎች በኋላ ዋናው አብራሪ ከእንቅልፉ በመነሳት ረዳት አብራውን እንቅልፍ እንደጣለው እና አውሮፕላኑም ከበረራ መስመሩ እንደወጣ መረዳቱ ተነግሯል።
በፍጥነት የስራ አጋሩን በመቀስቀስ ከጃካርታ ሲመጣላቸው ለነበረ ጥሪ ምለሽ በመስጠት አውሮፕላኑን ወደ ዋና መስመር መመለስ መቻሉም ነው የተገለተው።
ክስተቱ አገደኛ የበረራ ስህተት ቢሆንም፤ ኤር ባስ ኤ 320 አውሮፕላን ውስጥ ተሳፍረው የነበሩ 153 ተሳፋሪዎች እና 4 የበረራ ሰራተኞች 2 ሰዓት ከ35 ደቂቃ ከፈጀ በረራ በኋላ በሰላም ማረፍ ችለዋል ነው የተባለው።
የኢንዶኔዢያ የአየር ትራንስፖርት ዋና ዳይሬክተር ክሪስቲ እንዳህ ሙርኒ “ትራንስፖርት ሚኒስቴር ባቲክ ኤርን ያጋጠመውን ክስተት አጥብቆ ያወግዛል” ያሉ ሲሆን፤ በጉዳዩ ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።
ክስተቱ አየር መንገዶች የሰራተኞቻቸው የእረፍት ጊዜ ላይ የበለጠ ትኩረት እንዲሰጡ ጠይቀዋል።
ባቲክ ኤር በዛሬው እለት በሰጠው መግለጫ 'በቂ የእረፍት ፖሊሲ እንደሚከተል እና ሁሉንም የደህንነት ቅድመ ሁኔታዎች ተግባራዊ በማደረግ እንደሚሰራ አስታውቋል።
በጥር 25ቱ ክስተት የተሳተፉት አብራ እና ረዳት አብራሪ በጊዜያዊነት ከስራቸው መታገዳቸውንም ነው አየር መንገዱ ያስታወቀው።
ክስተቱን እየተከታተሉ ያሉ መርማሪዎች የአብራሪዎቹን ምንነት ከመግለጽ በቆጠቡም እድሜያቸው 32 እና 28 የሆነ የኢንዶኔዢያ ዜጎች ናቸው ብለዋል።
የኢንዶኔዥያ የትራንስፖርት ሚኒስቴር በአየር መንገዱ ላይ ምርመራ እንደሚከፍት በዛሬው እለት አስታውቋል።