የማላዊን ምክትል ፕሬዝደንት ይዞ ሲበር የነበረው አውሮፕላን የደረሰበት ጠፋ
የማላዊን ምክትል ፕሬዝደንት ይዞ ሲበር የነበረው ወታራዊ አውሮፕላን የደረሰበት የጠፋው በትናንትናው እለት ነው
የሀገሪቱ ፕሬዝደንት "አውሮፕለኑ እስከሚገኝ ድረስ ፍለጋው እንዲካሄድ ጥብቅ ትዕዛዝ ሰጥቻለሁ" ብለዋል
የማላዊን ምክትል ፕሬዝደንት ይዞ ሲበር የነበረው አውሮፕላን የደረሰበት ጠፋ።
የማላዊን ምክትል ፕሬዝደንት ይዞ ሲበር የነበረው ወታራዊ አውሮፕላን የደረሰበት የጠፋው በትናንትናው እለት ነው።
ምክትል ፕሬዝደንት የሆኑትን ሳውሎስ ቺሊማን ይዞ የጠፋው አውሮፕላን እስከሚገኝ ድረስ የፍለጋ እና ነፍስ የማዳን ዘመቻው እንደሚቀጥል የሀገሪቱ ፕሬዝደንት በቴሌቫዥን ባስተላለፉት መልእክት ተናግረዋል።
የ51 አመቱ ቺሊማ ከሌሎች ዘጠኝ ዘዎች ጋር ከዋና ከተማዋ ሊሎንግዌ ከጠዋቱ ሶስት ሰአት መነሳታቸውን የማላዊ ፕሬዝደንት እና የካቢኔ ቢሮ ባወጣው መግለጫ ማስታወቁን ሮይተርስ ዘግቧል።
እንደመግለጫው ከሆነ አውሮፕላኑ ከራዳር ውጭ ከሆነ በኋላ በአቬሽን ባለስልጣናት በኩል ግንኙነት ለመፍጠር የተደረገው ሙከራ አልተሳካም። አውሮፕላኑ በምዝዙ አውሮፕላን ማረፊያ ከአንድ ሰአት በኋላ እንዲያርፍ ይጠበቅ ነበር።
አውሮፕላኑ በነበረው ጭጋጋማ አየር ምክንያት ወደ ዋና ከተማዋ እንዲመለስ ታዞ እንደነበር ፕሬዝደንት ላዛሩስ ቻክዌራ ተናግረዋል።
"በህይወት ይተረፋሉ የሚል ትንሽ ተስፋ አለኝ" ያሉት ፕሬዝደንቱ ፍለጋው ከጫካው በ10 ኪሎሜትር ራዲየስ ውስጥ እየተካሄደ መሆኑን አክለው ገልጸዋል።
"አውሮፕለኑ እስከሚገኝ ድረስ ፍለጋው እንዲካሄድ ጥብቅ ትዕዛዝ ሰጥቻለሁ"
ፕሬዝደንቱ እንደገለጹት ማላዊ ጎረቤት ሀገራትን፣ አሜሪካን፣ እንግሊዝን፣ ኖርዌይን የእስራኤል መንግስትን በፍለጋ ጥረቷ እንዲረዷት ጠይቃለች።
በቀጣይ አመት በሚካሄደው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ እጩ ይሆናሉ ተብለው የሚጠበቁት ቺሊማ በፈረንጆቹ 2022 በሙስና ተጠርጥረው ታስረው ነበር።
ነገርግን የማላዊ ፍርድ ቤት የቀረበባቸውን ክስ ባለፈው ወር ውድቅ አድርጎታል።