በኳታር አየር መንገድ አውሮፕላን አየር ላይ ባጋጠመው መነዋወጥ 12 ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ
ቦይንግ 787 ድሪምላይር ከኳታር ዶሃ ወደ አየርላንድ በመበረር ላይ እያለ ነው ችግሩ ያጋጠመው
በአደጋውም መንገደኞች እና የበረራ አስተናጋጀች መጎዳታቸው ተነግሯል
የኳታር አየር መንገድ ንብረት የሆነ ቦይንግ 787 ድሪምላይር አውሮፕላን አየር ላይ ባጋጠመው መነዋወጥ 12 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ።
የደብሊን ኤርፖርት እንዳስታወቀው ከሆነ፤ በኳር አየር መንግድ አውሮፕላን ከዶሃ ወደ አየርላንድ በመጓዝ ላይ የነበሩ መንገደኞች አየር ላይ ባጋጠመ መነዋወጥ ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የበረራ ቁጥሩ QR017 የሆነ ቦይንግ 787 ድሪምላይር አውሮፕላን የመነዋወጥ አደጋው ካጋጠመው ከጥቂት ቆይታ በኋላ ማረፉንም የደብሊን ኤርፖርት አስታውቋል።
አውሮፕላኑ በሚያርፍበት ጊዜም የኤርፖርት ፖሊስና የእሳት አደጋ ሰራተኞችን ጨምሮ የአደጋ ጊዜ የአገልግሎት ሰጪ ሰራተኞች በስፍራው መድረሳቸው ተነግሯል።
አውሮፕላኑ አየር ላይ ባጋጠመው መነዋወጥም 6 መንገደኞች እና 6 የበረራ አስታናጋጆች በድምሩ 12 ሰዎች ላይ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት ማጋጠሙን ነው የደብሊን ኤርፖርት በመግለጫው ያስታወቀው።
የአየር ላንድ መገናኛ ብዙሃን መንገደኞችን ዋቢ አድርገው ባወጡት መረጃ፤ ክስተቱ ለ20 ሰከንድ መቆየቱ እና ምግብ እና መጠት በሚቀርበብተ ጊዜ ነው ያጋጠመው ብለዋል።
የኳታር አየር መንገድ ስለ ክስተቱ በሰጠው መግለጫ፤ ጥቂት ቁጥር ያላቸው መንገደኞች አየር ለይ መጠነኛ ጉዳት እንዳጋጠማቸው እና የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሆነ አስታውቋል።
በክስተቱ ዙሪያ ማብራሪያ ከመስጠት የተቆጠበው አየር መንገዱ፤ ውስጣዊ ምምርመራ ይደረግበታል ብሏል።
የኳታር አየር መንግድ አየር ላይ የመነዋወጥ አደጋ ያጋጠመው የሲንጋፖር አወሮፕላን ላይ ካጋጠመው ተመሳሳይ አደጋ ጋር በ5 ቀናት ልዩነት ውስጥ ነው።
211 ሰዎችን አሳፍሮ የነበረው የሲንጋፖር አየር መንግድ አውሮፕላን በገጠመው ችግር አንድ መንገደኛ ህይወቱ ማለፉና 30 ሰዎች መቁሰላቸው ይታወሳል።