በአሜሪካ ፊላዴልፊያ በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ የሁሉም ተሳፋሪዎች ህይወት ማለፉ ተነገረ
አነስተኛ የህክና አውሮፕላኑ ስድስት ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ ነበረ
በአሜሪካ ከሁለት ቀናት በፊት በደረሰ አስከፊ የአውሮፕላን አደጋ 67 ሰዎች መሞታቸው ይታወቃል
በአሜሪካ ፊላዴልፊያ ታካሚ አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አነስተኛ አውሮፕላን ተከስክሶ የሰዎች ህይወት ማለፉ ተነግሯል።
አነስተኛ አውሮፕላኑ በፊላደልፊያ ህክምና የተደረገላት የ5 ዓመት ህጻን ልጅ እና አስታማሚ እናቷን ወደ መኖሪያቸው በመለስ ላይ እያለ ነው የተከሰከሰው ተብሏል።
አነስተኛ የህክምና አውሮፕላኑ 6 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነረ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ አራቱ የአውሮፕላኑ ሰራተኞች ሰራተኞች፤ ቀሪዎቹ ታካሚ ህጻን እና አስታማሚ እናት መሆናቸው ነው የተገለፀው::
በአውሮፕኑ ውስጥ ተሳፍረው የነበሩ ሁሉም ሳይሞቱ እንዳልቀረም ነው የተነገረው።
አውሮፕላኑ መሃል ከተማ ላይ መከስከሱን ተከትሎም ተከትሎ ቤቶች እና ተሽከርካሪዎች በእሳት መያያዛቸውን የተነገረ ሲሆን፤ መሬት ላይ የነበሩ በርካታ ሰዎች እንደቆሰሉም ተነግሯል።
የፊዴራል አቪዬሺን አስተዳዳር (ኤፍ ኤ ኤ) እንዳስታወቀው ከሆነ አነስተኛ አውሮፕኑ ከተነሳ ከ30 ሴኮንድ በኋላ መከስከሱን አስታውቋል።
አሁን ላይ የአደጋው መንስዔ እየተጣራ መሆኑንም ነው ባለስልጣ ያስታወቀው።
የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ወደ ሰሜን ምስራቅ ፊላደልፊያ በማቅናት የነፍስ አድን ስራ እና በአደጋው የተከሰተው የእሳት አደጋ የማጥፋ ስራ እየተረባረቡ ነው::
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ የማህራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት በአደጋው ማዘናቸውን ገልጸው፤ ተጨማሪ ንጹህ ነብሶች አጥተናል ብለዋበ።
አሜሪካ ባለፈው አንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ ሶስት የአውሮፕላን አደጋ አጋጥሟታል::
ከሁለት ቀናት በፊት በዋሽንግን ከተማ አቅራቢያ የመንገደኞች አውሮፕላን ከወታደራዊ ሄሊኮፕተር ጋር አየር ላይ ተጋጭተው የ67 ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል።