ልዩልዩ
ችግኝ ተከላ ለሰላም
አሜሪካ ለብዙዓመታት ቆይተው የተመለሱት አቶ ጋሻው ጣሂር በችግኝ ተከላ ሰላምን መስበክ ከጀመሩ ሰነባብተዋል
በሚኖሩበት አሜሪካ የገጠማቸውን አንድ ክስተት መነሻ በማድረግ ፣ ‘ፕላንቲንግ ትሪ ፎር ፒስ’ (ለሰላም ዛፍ/ችግኝ መትከል) በሚል እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ በርካታ ችግኞችን የተከሉት አቶ ጋሻው አብደላ ጣሂር ለብዙ ኢትዮጵያውያን ፣ በተለይ ለዕናቶች የስራ ዕድልም ፈጥረዋል፡፡ በሙያቸው የግንባታ መሀንዲስ የሆኑት ጋሻው ስለ ችግኝ ተከላ ስራቸው በአሜሪካ የተለያዩ ትምህርት ቤቶችም ለተማሪዎች ግንዛቤ ይሰጣሉ፡፡ አሁንም እራሳቸው በመሰረቱት ‘ግሪን ላንድ ዴቨሎፕመንት ፋውንዴሽን’ አማካኝነት አቶ ጋሻው “ሰዎችን ሁሉ አንድ የሚያደርግ” ባሉት የችግኝ ተከላ ዘርፍ ስለ ሰላም ማወጃቸውንን ቀጥለዋል፡፡