ስፔናዊው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በምርጥ አሰልጣኝነት ለሽልማቱ በእጩነት ቀርቧል
ለፊፋ የምርጥ ተጨዋቾች ሽልማት በእጩነት የተመረጡት ታውቀዋል።
ሊዮነል ሜሲ፣ ክሊያ ምባፔ እና ኢርሊንግ ሀላንድ ከወንዶች ለፊፋ ምርጥ ተጨዋች ሽልማት እጩ ከሆኑት መካከል ሲሆኑ ከሴቶች ደግሞ በዓለም ዋንጫ የወርቅ ኳስ የተሸለመችው ስፔናዊቷ አልታና ቦንማቲ ለምርጥ ሴት ተጨዋችነት በእጩነት ከቀረቡት መካከል ትገኝበታለች።
- ክለቦች በተጠናቀቀው የግማሽ አመት የተጨዋቾች ዝውውር ክብረወሰን የሰበረ ወጭ ማውጣታቸውን ፊፋ ገለጸ
- ሊዮኔል ሜሲ ኢንተር ማያሚን የዋንጫ ባለቤት ለማድረግ መቃረቡን ተከትሎ በምርጫዬ 'ደስተኛ ነኝ' አለ
በወንዶች ተርታ ለእጩነት ከቀረቡት መካከል ከግማሽ ደርዘን በላይ የሚሆኑት በአስደናቂ ሁኔታ በ2022-2023 ድል ካደረገው የማንቸስተር ሲቲ ቡድን ውስጥ ሲሆኑ ስፔናዊው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ደግሞ በምርጥ የወንዶች አሰልጣኝነት በእጩነት መቅረቡን ሮይተርስ ዘግቧል።
በምርጥ የሴት ተጨዋችነት ከቀረቡት 16 እጩዎች መካከል የዘንድሮውን የሴቶች የዓለም ዋንጫ ካሸነፈው የስፔን ቡድን ውስጥ አራት ተጨዋቾች ይገኙበታል።
በዋንጫ ውድድሩ የብር ሜዳሊያ ያገኘችው እንግሊዝ አሰልጫኟ እና ሶስት ተጨዋቾቿ ለእጩነት ቀርዋል። የዓለም ዋንጫው ተባባሪ አዘጋጅ የነበረችው አውስትራሊያም ስሶት ተጨዋቾቿ በእጩነት ቀርበውላታል።
የዓለም ዋንጫው አሸነፊ ሊዮነል ሜሲ፣ የስፔኑ አሌክ ፑቴላስ የምርጥ ተጨዋች ሽልማት የወቅቱ ባለቤቶች መሆናቸው ይታወሳል።
የእጩዎች መረጣ የተካሄደው የቀድሞ ተጨዋቾች የሆኑትን ሚያ ሀም እና ዲድየር ድርግባን ባካተተ የባለሙያዎች ቡድን ነው ተብሏል።