ክለቦች በተጠናቀቀው የግማሽ አመት የተጨዋቾች ዝውውር ክብረወሰን የሰበረ ወጭ ማውጣታቸውን ፊፋ ገለጸ
ብራዚላያዊውን ኮከብ ኔማርን፣ የሴኔጋሉን አጥቂ ሳዲዮ ማኔን እና ብራዚላዊውን አማካኝ ተጨዋች ፋቢንሆን የመሳሰሉ ተጨዋቾች ለሳኡዲ ክለቦች ከፈረሙ በኋላ ሳኡዲ አረቢያ ለዝውውር ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ በማውጣት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች
የእስያ ክለቦች ለመጀመሪያ ጊዜ ከዓለም የተጨዋቾች ዝውውር ወጭ 14 በመቶ የሚሆነውን ሸፍነዋል ብሏል ፊፋ
ክለቦች በተጠናቀቀው የግማሽ አመት የተጨዋቾች ዝውውር ክብረወሰን የሰበረ ሰባት ቢሊዮን ዶላር ወጭ ማውጣታቸውን ፊፋ አስታውቋል።
ከፈረንጆቹ ሐምል 1 እስከ መስከረም 1 ድረስ የተመዘገው የዝውውር ወጭ ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር 47.2 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን በ2019 ከተመዘገው የግማሽ አመት ክብረወሰን ጋር ሲነጻጸር ደግሞ የ28.8 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ፊፋ ገልጿል።
"እንግሊዝ አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች... በዝውውሩ 1.89 ቢሊዮን ዶላር አውጥታለች። ወደ እንግሊዝ 449 ዝውውሮች የተከናወኑ ሲሆን ወደ ውጭ 514 ዝውውሮች መፈጸማቸውን" የፊፋ የህግ ከፍተኛ ባለሙያ ኢሚሎ ግራሽያ ሲልቨሮ ተናግረዋል።
ብራዚላያዊውን ኮከብ ኔማርን፣ የሴኔጋሉን አጥቂ ሳዲዮ ማኔን እና ብራዚላዊውን አማካኝ ተጨዋች ፋቢንሆን የመሳሰሉ ተጨዋቾች ለሳኡዲ ክለቦች ከፈረሙ በኋላ ሳኡዲ አረቢያ ለዝውውር ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ በማውጣት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
የእስያ ክለቦች ለመጀመሪያ ጊዜ ከዓለም የተጨዋቾች ዝውውር ወጭ 14 በመቶ የሚሆነውን ሸፍነዋል ብሏል ፊፋ።
ፈረንሳይ 859 ቢሊዮን ዶላር በማውጣት በተጨዋቾች ዝውውር ላይ ከፍተኛ ወጭ ካወጡ ሶስት ሀገራት እንዷ መሆን ችላለች።