ጠ/ሚ ዐቢይ ኢትዮጵያውያን ያለ አንዳች ማመንታት ኢትዮጵያን በአንድነት ከጥቃት እንከላከላት ሲሉ ጥሪ አቀረቡ
የጠላት የጥንካሬ ምንጭ የእኛ ድክመትና መዘናጋት በመሆኑ ነቅተንና ተባብረን ልንጠብቀው ይገባል" ብለዋል
ህዝቡ የክት ጉዳዩን ለጊዜው አቆይቶ ሕወሓት ለመመከት መዝመት አለበት ሲሉም ጥሪ አቅረበዋል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዘሬ ማምሻውን የሰሜን ኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ መግለጫ አውጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ሕወሓት፣የመጨረሻ አቅሙን አሟጥጦ ለማጥቃት የሚያደርገውን ጥረት መከላከጻ ሠራዊት በምድርና በአየር እየታገዘ እንዳይነሳ አድርጎ እየሰበረው ይገኛል ብለዋል።
ሕወሐት12 ዓመት ሕጻን እስከ 65 ዓመት አዛውንት ያገኘውን ሁሉ ሰብስቦ አዝምቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለድል ቋምጦ መጥቶ በወሎው ግንባር ሰፊ ቁጥር ያለው ኃይሉን ማጣቱን አስታውሰዋል።
በቀጣይ ጊዜያትም የተረፈውን ኃይል አሰባስቦ ተመሳሳይ ጥቃቶችን መሠንዘሩ አይርም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ "የጠላት የጥንካሬ ምንጭ የእኛ ድክመትና መዘናጋት እንደሆነ አውቀን ነቅተንና ተባብረን ልንጠብቀው ይገባል" ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም "በመካከላችን ሆኖ ለጠላት የሚሠራውን የሕወሐት ወኪል በንቃት መከታተል ያስፈልጋል፣ ለዘመናት ከጠላት ጋር የጥቅም ትስስር የፈጠሩ ሰዎች ዛሬም በጉያችን ሆነው የጠላትን ምኞት ከዳር ለማድረስ ደፋ ቀና ይላሉ፣ ስለዚህ ሁሉም ዜጋ ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን የጠላት ወኪሎችን ማጋለጥ ይገባል" ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"ሀገርን ከጥቃት የመከላከል ኃላፊነት የጥቂቶች ሳይሆን የሁላችንም ነው፣ እያንዳንዱ ዜጋ ከእኔ ምን ይጠበቃል? እኔ ምን እያደረኩ ነው? ማለት አለበት" ብለዋል።
ስለዚህ መላው የሀገሪቱ ህዝብ የክት ጉዳዩን ለጊዜው አቆይቶ፣ ለማጥፋት የመጣውን ሕወሓት ለመመከት፣ ለመቀልበስና ለመቅበር ማናቸውንም መሣሪያና ዐቅም ይዞ፣ በሕጋዊ አደረጃጀት መዝመት አለበት ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።