በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ግልጽነት የተሞላበት ውይይት አድርገናል”ብለዋል
ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ-ባይደን ጋር በስልክ መወያየታቸውን አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ባወጡት መረጃ፤ ከፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር በነበራቸው የስልክ ቆይታ
“በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች፣ በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ግልጽነት የተሞላበት ውይይት አድርገናል”ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒሰትሩ በጋራ በመከባበር ላይ የተመሰረተ ገንቢ ምክክር ማደረጉ ትልቅ ጥቅም ያለው በመሆኑ የሀገራቱን ትብብር ለማጠናከር ተስማምተናል ሲሉም አክለዋል።