ጆ ባይደን፤ ከ110 ሃገራት መሪዎች ጋር ለማካሄድ ባሰቡት የበይነ መረብ ጉባዔ ጠ/ሚ ዐቢይን ሳያካትቱ ቀሩ
ሩሲያ ሃገራትን ለመከፋፈል የሚደረግ ነው ስትል የባይንን እርምጃ ኮንናዋለች
ባይደን በጉባዔው ታይዋንን መጋበዛቸው ቻይናን አስቆጥቷል
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዴሞክራሲን በተመለከተ በመጪው ታህሳስ ወር ሊያካሂዱ ላሰቡት የበይነ መረብ ጉባዔ የ110 ሃገራት መሪዎችን ጋበዙ፡፡
ጉባዔው በዋናነት “ዴሞክራሲያዊ እና አምባገነን” የሚሉ እሳቤዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት በፈረንጆቹ ታህሳስ 9 እና 10/ 2021 የሚካሄድ ነው፡፡
ባይደን እነዚህ እሳቤዎች ለውጭ ግንኙነት ፖሊሲያቸው መቃኛ እንደሚሆኑ ቀደም ሲልም ሲያስታውቁ ነበር፡፡
“ከእንግዲህ እኔ መከላከያን በግንባር ሆኜ ለመምራት ከነገ ጅምሮ ወደ ትግሉ ሜዳ እዘምታለሁ”- ጠ/ሚ ዐቢይ
በጉባዔው በቀዳሚ የአሜሪካ ተፎካካሪነታቸው የሚታወቁት ሩሲያ እና ቻይና አልተጋበዙም፡፡ ሩሲያ ሃገራትን ለመከፋፈል የሚደረግ ነው ስትል የባይንን የጉባዔ ጥሪ ኮንናዋለች፡፡
ቻይና ደግሞ የግዛቷ አካል አድርጋ የምታስባት ታይዋን በጉባዔው እንድትሳተፍ በመጋበዟ ተቆጥታለች፡፡
ከአፍሪካ አንጎላ፣ ቦትስዋና፣ ጋና፣ ሞሪሽዬስ፣ ናሚቢያ፣ ሴኔጋል፣ ሲሼልስ፣ ዛምቢያ፣ ዲ.አር ኮንጎ፣ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያ እና ኒጀር ናቸው የተጋበዙት፡፡
ኢትዮጵያ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኩል በወጣው የተጋባዦች ዝርዝር ውስጥ አልተካተተችም፡፡
ጠ/ሚ/ር ዐቢይ መላው ጥቁር ሕዝብ ከኢትዮጵያ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቀረቡ
ከመካከለኛው ምስራቅ እስራኤል እና ኢራቅ ብቻ ናቸው የተሳተፉት፡፡ የቀጣናው የአሜሪካ የቅርብ አጋር የሆኑት የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ግብጽ፣ ዮርዳኖስ ኳታር ጭምር አልተጋበዙም፡፡
ከደቡብ አሜሪካ በጃይር ቦልሶናሮ የምትመራውን ብራዚልን ጨምሮ ኡራጓይን የመሳሰሉ የቀጣናው ሃገራት ተጋብዘዋል፡፡
ህንድ፣ ፓኪስታን፣ ማልዲቭስ እና ኔፓል ከእስያ የጉባዔው ተሳታፊዎች ናቸው፡፡