ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሰሞኑንን ከኃላፊነት በተሰኑት የካቢኔ አባላት ምትክ ሹመት ሰጡ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ማሞ ምሕረቱን በዶ/ር ይነገር ደሴ ምትክ የብሔራዊ ባንክ ገዢ አድረገው ሾሟል
ዶ/ር አለሙ ስሜ በወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ምትክ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል
ሰሞኑን አራት ከፍተኛ የመንግስት ሹመኞች ከኃላፊነታቸው ተነስተው የሚንስትሮች ምክር ቤት የሽኝት በመርሀ-ግብር አዘጋጅቶ መሸኘታቸው የሚታወስ ነው።
ጠቅላይ ሚነስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት መርሃ-ግብር ሽኝት የተደረገላቸው ሚኒስትሮች የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚንስትር ዳግማዊት ሞግስ፣ የማዕድን ሚንስትር ታከለ ኡማ፣ የግብርና ሚንስትር ኡመር ሁሴን እና የጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ኃላፊ ተፈሪ ፍቅሬ ነበሩ፡፡
የጠቅላይ ሚነስትር ጽ/ቤት ዛሬ ይፋ ባደረገው መረጃ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከኃላፊነታቸው በተነሱት ሚኒስትሮች ምትክ ሹመቶች መስጠታቸው አስታውቋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዶ/ር አለሙ ስሜን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር፣ ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝን የማዕድን ሚኒስትር፣ ዶ/ር ግርማ አመንቴን የግብርና ሚኒስትር አድረገው የሾሙ ሲሆን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዲሱን ሹመት እንዲያጸድቅ ጠይቀዋል፡፡
በተጨማሪም ከጥር 10፣ 2015 ጀምሮ አቶ ማሞ ምሕረቱ - የብሔራዊ ባንክ ገዢ፣ ወ/ሮ አለምጸሐይ ጳውሎስ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር፣ ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር፣ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴን የውጭ ፖሊሲ አማካሪ ሚኒስትር፣ አቶ መለሰ አለሙን በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ የዘርፍ አስተባባሪ አድረገው ሾሟል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡