ፖለቲካ
አራት ከፍተኛ የመንግስት ሹመኞች ከኃላፊነታቸው ተነሱ
የማዕድን ሚኒስትር ኢ/ር ታከለ ኡማና የትራስፖርት ሚኒሰትር ዳግማዊት ሞገስ ከተሸኑ ሹመኞች መካከል ናቸው
የግብርና ሚንስትሩ ኡመር ሁሴንና የጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ኃላፊ ተፈሪ ፍቅሬ በቅርቡ የአምባሳደርነት ተሹመዋል
የሚንስትሮች ምክር ቤት ዛሬ የጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ኃላፊን ጨምሮ ለሦስት ሚንስትሮች የሽኝት በመርሀ-ግብር አካሂዷል።
በሽኝት መርሃ ግብሩ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድና ምክር ቤቱ አባላት በተገኙበት በዛሬው እለት ተካሂዷል።
የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚንስትር ዳግማዊት ሞግስ፣ የማዕድን ሚንስትር ታከለ ኡማ፣ የግብርና ሚንስትር ኡመር ሁሴን እና የጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ኃላፊ ተፈሪ ፍቅሬን ዛሬ መሸኘታቸውን የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት አስታውቋል።
የግብርና ሚንስትር ኡመር ሁሴንና የጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ኃላፊ ተፈሪ ፍቅሬ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በቅርቡ የአምባሳደርነት ሹመት ከሰጧቸው አዲስ አምባሳደሮች ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል።
የዳግማዊት ሞገስና ታከተ ኡማ ቀጣይ ሹመት እስካሁን ባይረጋገጥም፤ መንግስት ለአዲስ 14 አምባሳደሮች ሹመት መስጠቱን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ከሰሞኑ ተናግረዋል።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለአራቱ የምክር ቤት አባላት ቀጣይ ጉዟቸው ስኬትን ተመኝቷል።