ጠ/ሚ ዐቢይ በነቀምቴ ወለጋ ስታዲየም ንግግራቸው ያነሷቸው አንኳር ነጥቦች ምንድን ናቸው?
ጠ/ሚ ዐቢይ በንግግራቸው ሠላም፣ አንድነትና ልማትን ማረጋገጥ ላይ ያተኮሩ ሀሳቦችን አንስተዋል
“ጦርት፣ እርስ በእርስ መገዳድልና መበላላት ይብቃን” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጥሪ አቅርበዋል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) “ጦርት፣ እርስ በእርስ መገዳድልና መበላላት ይብቃን” ሲሉ ጥሪ አቀረቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትናንትናው እለት በነቀምቴ ወለጋ ስታዲየም በተዘጋጀ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ሠላም፣ አንድነትና ልማት ላይ ያተኮሩ ሐሳቦችን አንስተዋል።
በዚህም “የኦሮሞ ህዝብ ከአንድ ክፍለ ዘመን በለይ ማንነቱን ተነፍጎ፣ በቋንቋው መጠቀም አንዳይችል ተደርጎ፣ የሀገር ባለቤትነቱ ተነፍጎ በሀገሩ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ለመቆጠር ተገዶ ቆይቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒትር ዐቢይ፤ አሁን ግን በከተፈለ መሰዋእትነት “ኦሮሞ ነጻ ወጥቷል” ህዝቡ ይህንን ሊረዳ ይገባል ብለዋል።
“ለኦሮሞ ህዝብ በሙሉ በነቀምት አዋጅ ማወጅ እፈልጋለሁ” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በኦሮሚያ ምድር ውስጥ ጦርነት፣ የኦሮሞ ልጆች እርስ በእርስ በእርስ መገዳደል አንዲሁም የኦሮሞ ልጆች ተቀምጠው ስለ ችግሮቻቸው መወያየት አለመቻል ከዛሬ ጀምሮ መቆም ለአበት” ሲሉ ተናረዋል።
“በጠላት መታለል እና በጠላት አጀንዳ መከፋል ይብቃን” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ “ባህላችንን እና ማነታችንን የሚገልጸው በመወያት፣ በመደማመጥ እንዲሁም በጋራ የወሰኑትን ነገር ይዞ ወደ ስራ በመቀየር ነው” በማለት ገልጸዋል።
“አብረን መወያት አቅቶን ከጠላት ጋራ መምከር አሳፋሪ ነው፤ ስለዚህ ከታሪክ ተምረን ለህዝባችን ሰላም ማምጣት አንድንችል ጦርት እና መገዳደል ይብቃ” ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በንግግራቸው ያስተላለፉት ሌላኛው መልእከት ስለ አንድነት ሲሆን፤ “የኦሮረሞ ህዝብ ከአንድ ከፍል ዘመን በላይ በማንም ሲገዛ እና የማንም መጫወቻ ሲሆን የቆየው አንድነት ስላጣ ነው” ብለዋል።
“የኦሮሞ ህዝብ በአንድንት መቆም ቢችል ኖሮ ላለፉት 50 ዓመታት የኦሮሞ ህዝብ ትግል ወደኋላ እየተመለሰ አይኖርም ነበር” ሲሉም ተናግረዋል።
“ለልማትም፣ ለጦርነትም፣ ራስን ለመጠበቅም እንዲሁምየተለያዩ ሃሳቦችን ለማመንጨት አንድነት ያስፈልገናል” ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ “የኦሮሞ ህዝብ አንድንት ከማንኛመው ጊዜ እስፈላጊ የሚሆንበት ጊዜ ላይ ነን” ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በንግግራቸው ያነሱት ሶስተኛው ነጥብ ስለ ልማት ሲሆን በዚህም የለውጡ መንግስት ወደ ስልጣን ሲመጣ ሀገሪቱ ለሰራተኞቿ ደመወዘወ መከፍል የማትችልበትና የውጭ ሀገራት እዳዋ ከእቅሟ በላይ ነበር ሲሉ አስታውሰዋል።
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እንደ ምስራቅ አፍሪካ 2ኛ ነበር፤ እንደ አፍሪካም እኮኖሚያችን በጣም ወደ ኋላ የቀረ ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “ዛሬ ግን በጦርነት እና በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ሆነንመ ቢሆን በመስራቅ አፍሪካ 1ኛ፤ በአፍሪካ ውስጥም ከፍተኛ የኢኮኖሚ ለውጥ እየገነባን ነው” ብለዋል።
“የአፍሪካ ተምሳሌት የሚሆን ኢኮኖሚ እና ብልጽግናን የመገንባት ስራችንን የሚያቆምን ምንም ምድራዊ ኃይል የለም” ሲሉም ተናግርዋል።
“ዛሬ ከነቀምት በማውጀው አዋጅ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ መረዳት ያለበት የኦሮሞ አንድነት የማይጠበቅ ከሆነ የኢትዮጵያ አንድነት ሊጠበቅ አይችልም። ኦሮሞ ሠላም ካልሆነ ኢትዮጵያ ሠላም አይኖራትም። ኦሮሞ ታላቅ ነው። ራሱን ለውጦ አገር ይለውጣል” በማለት ተናግረዋል።
“እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሰጠውን ማብቂያ የሌለው ሰላም ለኢትዮጵያ አውጃለሁ” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በንግግራቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አክለውም “የወለጋ ሕዝብ በሰላም እጦት ምክንያት በልማት በኩል ተጎድቷል፤ ወለጋን መቀየር እንፈልጋለን፤ ራዕይም አለን። ይህ ሀሳባችን በመንገድ ላይ እንዳይቀር ሕዝቡ እድል ይስጠን። ሕዝባችን እኛን ይደግፈን” ሲሉም ጥሪ አስተላልፈዋል።