ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፓትርያርክ አቡነ መርቆሪዎስ ህልፈተ ህይወት ማዘናቸውን ገለጹ
አቡነ መርቆሪዎስ ላለፉት 34 ዓመታት በፓትርያርክነት አገልግለዋል
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በ1980 ዓ.ም ነበር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ተብለው የተሰየሙት
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ህልፈተ ህይወት ማዘናቸውን ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተለያይተዋ የነበሩን ሁለት ሲኖዶሶችን አንድ እንዲሆኑ የጎላ አስተዋጽኦ ነበራቸው ብለዋል፡፡
“ተለያይተው የነበሩት ሁለቱ ሲኖዶሶች አንድ እንዲሆኑ ቅዱስነታቸው ወሳኙን ሚና መጫወታቸውን አስታውሳለሁ። ነገሮችን በአርምሞ እየተመለከቱ ሀገራችንን በጸሎት ያግዙ ነበር። በዚህ ወቅት እርሳቸውን ማጣት ከባድ ጉዳት ነው። ለሁላችንም መጽናናትን እመኛለሁ።”
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሰሞኑን ባደረባቸው ህመም የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ነበር፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በ1980 ዓ.ም ነሐሴ 29 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ተብለው የተሰየሙ ሲሆን ላለፉት 34 ዓመታት በፓትርያርክነት አገልግለዋል።
ፓትርያርኩ ከኢትዮጵያ በስደት ከወጡ በኋላ በአሜሪካን ለረጅም ጊዜ ከሳለፉ በኃላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ነበር ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት፡፡