ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መከላከያ ከትግራይ መውጣት የጀመረው “ከአንድ ወር በፊት” መሆኑን ገለጹ
መከላከያ ከወጣ በኋላ የትግራይ ኃይሎች መቀሌን ጨምሮ ሌሎች ከተሞችን መያዛቸው ተዘግቧል
መንግስት ጦሩን ከትግራይ ያስወጣው ቀውሱን በወይይት ለመፍታት በመፈለጉ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መከላከያ ከትግራይ ክልል መውጣት የጀመረው “ከአንድ ወር በፊት” በሆኑን ተናገሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህን ያሉት በዛሬው እለት ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት በ2014 ዓ.ም በጀትና በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደተናገሩት ከሆነ መንግስት መከላከያን ከትግራይ ያስወጣው ለወራት ወይይት ከተካሄደ በኃላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
መንግስት መከላከያ ሰራዊትን ከትግራይ ያስወጣው በ4 ዙር መሆኑን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒትስሩ ጦር መውጣት የጀመረው በግልጽ በማይታወቅበት ሁኔታ ነው ብለዋል፡፡
ሰራዊቱ በአራት ግንባር ተሰማርቶ የነበረ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከ15ቀናት በፊት ሰፊ ኃይል ከትግራይ መውጣቱን ገልጸዋል፡፡ መንግስት በ3ኛ ዙር ከተንቤን አካባቢ ሲፊ የመከላከያ መኪና (ኮንቪይ)ማስወጣት ሲጀምር መንገድ የዝጋት ሙከራ መከሰቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መውጣት ግልጽ የሆነው በ4ኛ ዙር ከመቀሊ ሲወጣ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መከላከያ ከመቀሌ ከውጣ በኋላ ለ2ቀናት መቀሌ አለመግባቱን ተግረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ መከላከያ ከትግራይ የወጣው በመንግስት ምክንያት እርሻ እንዳይስተጓጎልና የሰብአዊ እርዳታ አልደረሰም እንዳይባል፤ እንዲሁም ለህዝቡና ለሌሎችም አካላት የጥሞና ጊዜ ለመስጠት ነው ብለዋል፡፡
መንግስት መከላከያን ከትግራይ ያስወጣው ተሸመንፎ አለመሆኑን በፖለቲካዊ ውሳኔ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በአሁኑ ወቅት የህወሓት ኃይሎች መቀሌንና ሌሎች የክልሉን ከተሞች መቆጣጠራቸውና የክልሉን መሬት በሙሉ ለመያዝ እንደሚንቀሳቀሱ ማቀሳቸውን ሮይተርስ ዘግቦ ነበር፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም ከሳምንት በፊት ያወጃ ሲሆን ህወሓት ለተኩስ አቁም አልተገዣም፤ ተኩስ ከፍቷል ሲል ከሷል፡፡
መንግስት ተኩስ አቁም ያወጀው የትግራይን ቀውስ ጉዳይ በውይይት ለመፍታት ማቀዱን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ለዲፕሎማቶች ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት መናገራቸው ይታወሳል፡፡
የተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊና የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ ሮዝመሪ ዲካርሎ መንግስት ያስተላላፈው የተከስ አቁም ውሳኔ ህወሓትን ጨምሮ ሁሉም ወገኖች ሊጠቀሙበት የሚገባ እድል ነው፤ የህወሓት ኃይሎችም ተኩስ አቁሙን “በአስቸኳይና ሙሉ በሙሉ” ሊደግፉት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡