ሞዲ በኤምሬትስ ሰባተኛውን ይፋዊ ጉብኝታቸውን እያደረጉ ነው
የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር አቡዳቢ ሲደርሱ የአረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አቀባበል አድርገውላቸዋል
ሞዲ በቆይታቸው በአቡዳቢ የተገነባውን የሂንዱ ቤተመቅደስ ይመርቃሉ ተብሏል
የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለሁለት ቀናት ጉብኝት ኤምሬትስ ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቡዳቢ ሲደርሱ የአረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
أنا ممتن للغاية لأخي صاحب السمو @MohamedBinZayed، على الوقت الذي أمضيه في استقبالي في مطار أبو ظبي.
— Narendra Modi (@narendramodi) February 13, 2024
وإنني أتطلع إلى زيارة مثمرة من شأنها تعزيز الصداقة بين الهند والإمارات العربية المتحدة. pic.twitter.com/VltQVXgdxG
በኤምሬትስ ሰባተኛውን ይፋዊ ጉብኝታቸውን እያደረጉ የሚገኙት ናሬንድራ ሞዲ፥ በአቡዳቢ የተገነባውን የሂንዱ እምነት ቤተመቅደስ ይመርቃሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤተመቅደሱ እንዲገነባ ከፍተኛ ሚና የተጫወቱትን ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድን አመስግነዋል።
ጠንካራ ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ያላቸው ኤምሬትስ እና ህንድ በተለይ ናሬንድራ ሞዲ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ግንኙነታቸው ይበልጥ እየጎለበተ ይገኛል።
የሀገራቱ መሪዎች በአቡዳቢ በሚያደርጉት ምክክርም በኢነርጂ፣ በወደብ ልማት፣ በባቡር እና በዲጂታል መሰረተልማት ትብብራቸውን ማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ይወያያሉ።
መሪዎቹ ከሁለትዮሽ ጉዳዮች ባሻገር በቀጠናዊና አለማቀፋዊ ወቅታዊ ጉዳዮች እንደሚመክሩም ተገልጿል።
የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የኢምሬትስ ጉብኝታቸውን ሲያጠናቅቁ ወደ ኳታር ያቀናሉ።