የገቢዎች ሚኒስቴር ኢኮኖሚው እንዲነቃቃ በማሰብ የግብር እዳ ስረዛና ማበረታቻ ማድረጉ ሆቴሎችንም ተጠቃሚ አድረጓል
የገቢዎች ሚኒስቴር ኢኮኖሚው እንዲነቃቃ በማሰብ የግብር እዳ ስረዛና ማበረታቻ ማድረጉ ሆቴሎችንም ተጠቃሚ አድረጓል
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የሆቴል ዘርፉ ኪሳራ ውስጥ መግባቱንና መግንስት ዘርፉን ከኪሳር እንዲታደገው ጥያቄዎች ማቅረባቸውን የኢትዮጵያ ሆቴልና መሰል አገልግሎቶች አሰሪዎች ፌደሬሽን ገልጾ ነበር፡፡
የፌደሬሽኑ ፕሬዘዳንት ፍትህ ወልድሰንበት የታክስ መክፈያ ጊዜ እንዲራዘምላቸው፣ ባንክ የሰጣቸው ብድር ያለወለድ እንዲቆይላቸው፤ለባንክ የሚከፍሉት ወርሀዊ የብድር ክፍያ የመክፈያ ጊዜው አንዲራዘምና ያለወለድ ብድር እንዲሰጣቸውም ጠይቀው ነበር፡፡
በገጠማቸው ኪሳር ምክንያት፣ ሆቴሎቹ ለሰራተኞች ደሞዝ መክፈል እንደተቸገሩም አቶ ፍትህ በወቅቱ ገልጸው ነበር፡
የተመለሱ ጥያቄዎች
የፌደሬሽኑ ፕሬዘዳንት ፍትህ ወልደሰንበት መንግስት ለሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ለስራ ማስኬጃና ለደሞዝ የሚሆን ብድር መንግስት ፈቅዷል ብለዋል፡፡ የተጠየቀው ለአንድ አመት የሚሆን 6.6 ቢሊዮን ብር ቢሆንም መንግስት ማበደር የቻለው ለስድስት ወር የሚሆን የ3.3 ቢሊዮን ብር መሆኑን የፌደሬሽኑ ፕሬዘዳን አቶ ፍትህ አብራርተዋል፡፡
ሌላው የተመለሰው ጥያቄ፣ የግብር የእሮይታ ጊዜ ይሰጥን የሚለው ነበር፡፡በሆቴልና መሰል ዘርፍ የተሰማሩ የንግድ ተቋማት ክስ ላይ ያሉ ክሳቸው እንዲቋረጥና እስከ 2007 ዓ.ም ያለው የግብር እዳው እንዲሰረዝላቸው ሆኗል ያሉት ፕሬዘዳንቱ ሁሉም ክልሎች ላይ ተግባራዊ ስለመደረጉ እንዳማያውቁ ግልጸዋል፡፡ በአማራ ክልል ግን የታክስ እፎይታው ተግባራዊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በተጫማሪም ሰራተኛ ግብር እንዲቀር ተደጓል፤ የሰራተኛ የጡረት መዋጮ ግን ስለማይቀር ብድሩ ሲደርስ ከሐምሌ በኋላ እንዲከፈል ተወስኗል ብለዋል አቶ ፍትህ፡፡
ያልተመሱ ጥያቄዎች
መንግስት እስከሁን ያልመለሰው ጥያቄና ምንልባትም የሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን በዋናነት ሊታደጋቸው የሚችለው ሆቴሎች ብድር የሚከፍሉበት ጊዜ እንዲራዘም የጠየቁት ሲመለስ መሆኑን አቶ ፍትህ ገልጸዋል፡፡ ነገርግን ይህ ጥያቄ እስካሁን አልተመለሰም ብለዋል ፕሬዘዳንቱ፡
አቶ ፍትህ ከዚህ በፊት ከአል ዐይን አማርኛ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳሉት አብዛኞቹ ሆቴሎች በባክን ብድር የተሰሩ ናቸው፤ የየቀን ገቢያቸውን ለወርሀዊ የብድር ክፍያ እያዋሉት ስለሆነ እዳቸው ላይ ሊኩድ ካሽ/ የሚከፈል ብር/ እጥረት አጋጥሟቸዋል ብለው ነበር፡፡
ፕሬዛዳንቱ እንዳሉት ብድር የሚከፍሉበት ጊዜ ቢራዘምላቸው (ምሳሌ 10 አመት ከሆነ ወደ 20 አመት)፤ በየወሩ የሚከፍሉተ ወርዊ ክፍያ ስለሚቀንስላቸው ከኪሳራ ለማገገም የሚወስድባቸውን ጊዜ እንደሚያሳጥረውና ዘርፉን ከኪሳራ አንደሚታደገው ገልጸዋል፡፡ የብድር ወለዱም ለአንድ አመት እንዲተው/ፈሪዝ/ እንዲሆን እንደሚፈልጉና፣ይህ ጥያቄ እንዳልተመለሰላቸው አቶ ፍትህ ተናግረዋል፡፡
እንደ አቶ ፍተህ ገለፃ መንግስት የሰጠው ብር 3.3 ቢሊዮን ብር ሆቴሎቹ ደንበኛ በሆኑባቸው ባንኮች በኩል ብድሩ ይደርሳቸዋል ብለዋል፡፡ በመጀመሪያ ብድሩ ሊከፋፈል የታሰበው በልማት ባንክ በኩል ነበር ያሉት አቶ ፍትህ ልማት ባንክ መያዣ ስለሚፈልግ በንግድ ባንኮች በኩል እንዲከፋፈል መወሰኑን ገልጸዋል፡፡
እንደ አቶ ፍትህ ገላጻ ቀሪዎቹ ጥያቄዎች ለባንኮች ቀርበው ባንኮቹ እያዩቸው ነው፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር ዉሳኔ
የገቢዎች ሚኒስቴር በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተቀዛቀዘውን ኢኮኖሚ ለማበረታት በማሰብ ግብር ከፋዮች የግብር መክፈያ ጊዜ እንዲራዘምላቸው፤ ግብሩ አንዲሰረዝላቸውና የሚከፍሉት ደግሞ ማበረታቻ አንዲሰጣቸው ወስኗል፡፡
ከዚህ ውሳኔ ሆቴሎችን መሰል ተቋማትም ተጠቃሚ መሆናቸውን አቶ ፍትህ አስረድተዋል፡፡
የገቢዎች ሚኒስትር ላቀ አያሌው ከሁለት ሳምንት በፊት በሰጡት መግለጫ ድርጅቶች ሰራተኞቻቸውን እንዳያሰናብቱና አከራዮች ተካራዮቻቸውን አንዳያሶጡ ሲታወጅ፤ ድርጅቶች እንዳይዘጉ መንግስት የራሱን ድርሻ መወጣት ስላለበት ነው ይህን ያደረገው ብለዋል፡፡
አቶ ላቀ እንደገለጹት እስከ 2007 ድረስ የግብር እዳ ያለባቸው የንግድ ተቋማት ሙሉ በሙሉ ተሰርዞላቸዋል፡፡
ከ2008-2011ዓ.ም ድረስ ታክስ ተወስኖ የታክስ ማስታወቂያ የደረሳቸው ግብር ከፋዮች ያለባቸው መቀጫና ወለድ ከሆነ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይሰረዝላቸዋል፡፡ መቀጫ፣ ፍሬ ግብርና ወለድ ያለባቸው ደግሞ የፍሬ ግብሩን ብቻ 25 በመቶውን እስከ ግንቦት 28 የሚከፍሉ ከሆነ መቀጫና ወለዱ ይነሳላቸዋል ብለዋል አቶ ላቀ፡፡ ግብር ካፋዮች ፍሬ ግብሩን በአንድ ወር ግዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ የሚከፍሉ ከሆነ መቀጫና ወለድ ማንሳት ባሻገር ከፍሬ ግብሩ ላይ 10 በመቶ ይቀንስላቸዋል፡፡
መንግስት ምን ገምግሞ ነበር?
መንግስት የሆቴልና መሰል አገልግሎት ዘርፉን በኮረና ቫይረስ ምክንያት በከፍተኛ ደረጃ ይጎዳሉ ከሚባሉት ዘርፎች መካከል መድቦት ነበር፡፡
የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ የሆቴልና ቱሪዝም ጨምሮ ሁሉም ዘርፎች ተጋላጭ የሚሆኑባቸው ጉዳዮች ተለይተዋል፤ ኢኮኖሚዊ የመፍትሄ ምላሽም ተዘጋጅቷል” ብለው ነበር፡፡
አቶ አህመድ ተጋላጭ ለሆኑ ሴክተሮች/ዘርፎች/ በግል ንግድ ባንኮች በኩል ብድር እንዲደርሳቸው በብሄራዊ ባንክ በኩል የ15 ቢሊዮን ብር ቀርቧል መቅረቡንም ገልጸው ነበር፡፡ በዚሁ መሰረት መንግስት ለሆቴሎች የብድር አቅርቦት አመቻችቷል፡፡