ፕሬዝዳንት ፑቲን በቡድን 20 አባል ሀገራት ጉባኤ ላይ እንደሚሳተፉ አረጋገጡ
የዘንድሮው የቡድን 20 አባል ሀገራት ጉባኤ ከከአራት ወራት በኋላ በሲንጋፖር ይካሄዳል
የምዕራባዊያን ሀገራት መሪዎች ፕሬዝዳንት ፑቲንን ማግኘት እንደማይፈልጉ መናገራቸው ይታወሳል
ፕሬዝዳንት ፑቲን በቡድን 20 አባል ሀገራት ጉባኤ ላይ እንደሚሳተፉ አረጋገጡ፡፡
ሩሲያ በዩክሬን እያካሄደችው ባለው ጦርነት ምክንያት አሜሪካን እና የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ በርካታ ሀገራት በሩሲያ ላይ ማዕቀቦችን በመጣል ላይ ናቸው፡፡
እስካሁን በሩሲያ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦች ብዛት ከስድስት ሺህ በላይ የደረሰ ሲሆን ሩሲያም ተመሳሳይ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ትገኛለች፡፡
ይህ በዚህ እንዳለም ሩሲያን ከዓለም መድረኮች ሁሉ የመነጠሉ ስራ በምዕራባዊያን የቀጠለ ሲሆን የፊታችን ህዳር በኢንዶኔዥያ አስተናጋጅነት የቡድን 20 አባል ሀገራት ጉባኤ እንደሚካሄድ ይጠበቃል፡፡
የዚህ ቡድን አባል የሖነችው ሩሲያ በጉባኤው ላይ በማን እንደምትወከል ከዚህ በፊት ያልተገለጸ ሲሆን አሜሪካንን ጨምሮ የአውሮፓ እና እስያ ሀገራት ፕሬዝዳንት ፑቲን በመድረኩ ላይ እንዳይገኙ ሲጠይቁ ቆይተዋል፡፡
አስተናጋጇ ኢንዶኔዥያም ሁሉንም የቡድን 20 አባል ሀገራትን በጉባኤው ላይ እንዲገኙ ግብዣ ያቀረቡ ሲሆን ሩሲያም ተጋብዛለች፡፡
ፕሬዝዳንት ፑቲንም በጉባኤው ላይ ለመገኘት ከኢንዶኔዥያ የቀረበላቸውን ግብዣ መቀበላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ከሰሞኑ የጀርመን ፕሬዝዳንት ኦላፍ ሾልዝ በኢንዶኔዥያው ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ገና እንዳልወሰኑ ተናግረው ምክንያታቸው ደግሞ ፕሬዝዳንት ፑቲን ከተገኙ ላለመገኘት መፈለጋቸው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
አሁን ላይ በጉባኤው ለመሳተፍ ግብዣውን የተቀበሉት ፕሬዝዳንት ፑቲን ተሳትፏቸው በአካል ይሁን በበይነ መረብ የሚለውን እንዳልወሰኑ ተገልጿል፡፡
የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሊን በበኩላቸው ፕሬዝዳንት ፑቲን በኢንዶኔዥያው የቡድን 20 ሀገራት ጉባኤ ላይ በአካል እንዲገኝ እንደሚፈልጉ ገልጸው ስለዩክሬን ጉዳይ ምን እንደሚያስቢ አይኑን እያየን በአካል መጠየቅ እንፈልጋለን ብለዋል፡፡