የሀገሪቱ መከላከያ መስሪያ ቤት ዘመቻው “ልዩ ትኩረት” የሚደረግለት ነው ብሏል
ሩሲያ ከዩክሬን ጋር እያካሄደችው ባለው ጦርነትና “ወታደራዊ ዘመቻ በዩክሬን” ብላ በሰየመችው ውጊያ የተሳተፉ ወታደሮችን ሸለመች።
የሀገሪቱ መከላከያ መስሪያ ቤት በጦርነት ለተሳተፉ ወታደሮች ሽልማት ሰጥቷል። የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌ ሾይጉ በወታደራዊው ተልዕኮው ለተሳተፉ የሀገሪቱ “ጀግኖች” ሽልማት ማበርከታቸው ተሰምቷል።
ሚኒስትር ሰርጌ ሺይጉ ወታደሮቹ ላደረጉት ብሔራዊ አገልግሎት ሽልማገት ከማበርከትም ባለፈ አጠቃላይ ሁኔታቸውን መገምገማቸው ተሰምቷል።
ነየሩሲያ ውጊያ አዛዦች አሁን በዩክሬን ላይ እየተወሰደ ላለው “ወታደራዊ ዘመቻ” የተቀናጀ ድጋፍ እንዲደረግ ሪፖርት ማቅረባቸው ተገልጿል።
ሚኒስትሩ መንግስታቸው ለዚህ ዘመቻ “ልዩ ትኩረትና ክትትል” እያደረገ መሆኑን ለወታደሮቻቸው መናገራቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ሩሲያ ቱዴይ (አርቲ ) ዘግቧል።
ከዚህ ባለፈም ሩሲያ ለወታደሮቹ የሚሆን ምቹ የኑሮ ሁኔታን ለመፍጠር ዝግጁ እንደሆነች ተናግረዋል። ይህ ድጋፍም ወታደሮቹ አሁን ባሉበት ጊዜያዊ የውጊያ ምሽጎች እንደሚደረግ ተገልጿል።
ሚኒስትሩ በስምሪት ላይ ላሉ ወታደሮች የሰጡት ሽልማት የወርቅ እንዲሁም ጅግንነትን ላሳዩ ዜጎች የሚሰጠውን የሩሲያ ብሔራዊ ሽልማትን ነው ተብሏል።