ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፡ መከላከያ በመጨረሻው ዘመቻ ሰላማዊ ሰዎችና ማህበራዊ ተቋማት እንዳይጎዱ ስልት ነድፏል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መከላከያ የመጨረሻ ዘመቻ እንዲፈጽም መታዘዙን ገለጹ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመጨረሻው የ72 ሰአት ገደብ ውስጥ “በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ልዩ ሃይሎችና ሚሊሺያ አባላት” እጅ መስጠታቸውን አስታወቁ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመጨረሻው የ72 ሰአት ገደብ ውስጥ “በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ልዩ ሃይሎችና ሚሊሺያ አባላት” እጅ መስጠታቸውን አስታወቁ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል እያካሄደ ያለውን “የህግ ማስከበር ዘመቻ” የመጨረሻ ምእራፍ እንዲያካሄድ መታዘዙን አስታውቀዋል፡፡
በፌደራል መንግስትና በትግራይ ክልል መካከል ያለው አለምግባባት ወደ ግጭት ያመራው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጥቅምት 24 ህወሓት በክልሉ በሚገኙት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ጥቃት መሰንዘሩንና በህወሓት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ከሳወቁ በኋላ ነው፡፡
ግጭቱ ከተጀመረ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በትግራይ በኩል ሆነው የትግራይ ልዩ ሃይል አባላትና ሚኒሻዎች በሰላም ለመከላከያ ሰራዊት እጅ እንዲሰጡ ሁለት የ72 ሰአታት የጊዜ ገደብ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሶስተኛ የ72 ሰአታት የጊዜ ገደብ መጠናቀቁንና በተሰጠው ጊዜ ውስጥ “በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ልዩ ሃይሎችና ሚሊሺያ አባላት እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊት” መስጠታቸውን ገልጸዋል፡፡
የ72 ሰአት ገደብ አላማው ህግ ማስከበርና ወንጀለኛውን የህወሓት ቡድን በአነስተኛ ዋጋ እጅ እንዲሰጥና “የህወሓት የጥፋት አላማ ዘይገቶም ቢሆን የገባው እንድ ሰው ህይወት ማዳን እንቻል ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመጨረሻው ዘመቻ ንጹሃን እንዳይጎዱ ጥንቃቄ ይደረጋል ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመቀሌ ከተማና ማህበራዊ ተቋማት እንዳይጎዱ ጥንቃቄ እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡
መከላከያ ሰራዊት ሰላማዊ ዜጎች በማይጎዱበት መልኩ ወንጀለኞችን ለመያዝ የሚያስችለውን ስልት ነድፏል፤ የመቀሌ ህዝብም ትጥቁን ፈቶ በቤቱ መቀመጥና ከወታደራዊ ኢላማዎች እንዲርቅ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በፌደራል መንግስትና በትግራይ ክልል መካከል ያለው ግጭት ከ20 ቀናት በላይ ሆኖታል፡፡