ኮሮና የሚያስከትለውን ችግር የምናልፈው በዝግጅታችን መጠን ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ“ወደፊት ምን ያጋጥመን ይሆን” የሚል ስጋት ስለሚኖር የስነ ልቦና ተጽእኖ ያሳድራል ብለዋል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኮሮና ቫይረስ የሚያስከትለውን ችግር “ያለ ከባድ ጫና ማለፍ የሚቻለው በዝግጅታችን መጠን ነው” ብለዋል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኮሮና ቫይረስ የሚያስከትለውን ችግር “ያለ ከባድ ጫና ማለፍ የሚቻለው በዝግጅታችን መጠን ነው” ብለዋል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኮሮና ቫይረስ የሚያስከትለውን ሀገራዊ ችግር ለማለፍ በችግሩ መጠን መዘጋጀት እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል፡፡
ጠቅላይ ሚነስትሩ በዛሬው እለት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ነገ ለሚከበረው የእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
“ይህ ያለንበት ወቅት ለኛ የተለየ ወቅት ነው፤ኮሮና ያለ ጦር መሳሪያ አለማችንን ወሯል፡፡ በሀገራችን ብዙዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤አንዳንዶችም ህይወታቸውን አጥተዋል”ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወረርሽኙ እስካሁን ካስከተለው የማህበራዊና ኢኮኖሚ ችግሮች ባሻገር ወደፊት የሚያስከትለው የስነልቦና ተጽእኖ እንደሚኖር ተናግረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “አሁን ከገጠመን የበለጠ ችግር እንዳይገጥመን እስከምን ድረስ መዘጋጀት እንዳለብን” መንግስትና ህዝብ በአንድ ልብ መስራት አለበቸው ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ክርስቲያኖች በአሉን በሚያከብሩበት ወቅት አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ ለቫይረሱ አጋላጭ ከሆኑ ድርጊቶች እንዲታቀቡም በመልእክታቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሁሉም የሚገባውን ከሰራ የችግሩ ጊዜ የከፋ ጉዳት ሳያስከትል ማሸነፍ እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡
መንግስት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር ለአምስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ ዘዋጅ በማወጅ የተለያዩ እግዶችን አውጦቶ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል፡፡
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ሶስት ሰዎች ሲሞቱ በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 105 ደርሷል፡፡