አዋጁ ከ“ህገ-መንግስታዊ አሰራር ወጥቶ” ለመስራት እንዳስፈለገው መንግስት ገለጸ
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለአምስት ወራት የሚቆይ መሆኑን ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ
ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለአምስት ወራት የሚቆይ መሆኑን ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ
ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለአምስት ወራት የሚቆይ መሆኑን ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ
ጠቅላይ አቃቤ ህግ ከሰአት በኋላ በሰጠው መግለጫ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከዛሬ ጀምሮ ለአምስት ወራት የሚቆይ መሆኑን አስታውቋል፡፡
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ በነበረው ስብስባ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየጨመረ በመምጣቱና መንግስት እስካሁን ከወሰዳቸው እርምጃዎች ተጨማሪ ውሳኔዎች በማስፈለጋቸው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን አስታውቋል፡፡
የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት “ከተለመደው ህገ-መንግስታዊ አሰራር ወጥቶ በልዩ ሁኔታ መንቀሳቀስ” እንደሚያስችል የገለጸው ጠቅላይ አቃቤ ህግ “የመንግስት ሥልጣን ላይ ያሉ ገደቦች ወይም የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች በተለየ ሁኔታ ለጊዜው ተፈጻሚነታቸው ቀርቶ በሙሉ ኃይል፣ በተቀላጠፈ እና በተቀናጀ መልኩ ለወረርሽኙ ምላሽ መስጠት” እንዲቻል አዋጁ ታውጇል ብሏል፡፡
በአወጁ የሚጣሉ “የመብት ገደቦች እና እርምጃዎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወስጥ ዘርዝሮ ማስቀመጥ ያልተቻለው” ገደቦቹና እርምጃዎቹ እንደ ወረርሽኙ ስርጭት በጊዜና ከቦታ ቦታ ስለሚለያዩ መሆኑን ጠቅለይ አቃቤ ህግ ገልጿል፡፡
በአስኳይ ጊዜ አዋጁ የተደነገጉ የመብት እገዳወችን የጣሰ ማንኛውም ስው እስከ ሶሰት አመት በሚደርስ ቀላል እስራትና ወይንም ከአንድ ሺህ እስከ ሁለት መቶ ሺህ እንሚያስቀጣ የወንጀል ህጉ ያስቀምጣል፡፡
በኢትዮጵያ እስካሁን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሁለት ሰዎች የሞቱ ሲሆኑ በቫይረሱ የተጠቁ ሶች ቁጥር ደግሞ ወደ 55 ከፍ ብሏል፡፡ በቫይረሱ ከተያዙት ሰዎች መካከል እስካሁን 4 ሰዎች አገግመዋል፡፡
የኮሮና ቫይረሰ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ መጋቢት 4፣ 2012 መገኘቱ ከተረጋገጠ በኋላ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎችና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ተገኝቷል፡፡